የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 1:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔም፥ “ወዮ​ልኝ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እነሆ ሕፃን ነኝና እና​ገር ዘንድ አል​ች​ልም” አልሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እኔም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዴት እንደምናገር አላውቅም፤ ገና ሕፃን ልጅ ነኝና” አልሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔም፦ “ወዮ! ጌታ አምላኬ፥ እነሆ፥ ብላቴና ነኝና እንዴት እንደምናገር አላውቅም” አልሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኔም፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ገና ልጅ ስለ ሆንኩ እንዴት እንደምናገር አላውቅም” ብዬ መለስኩለት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔም፦ ወዮ ጌታ እግዚአብሔር፥ እነሆ፥ ብላቴና ነኝና እናገር ዘንድ አላውቅም አልሁ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 1:6
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሙሴም መለሰ፥ “እነሆ፥ ባያ​ም​ኑኝ፥ ቃሌ​ንም ባይ​ሰሙ፦ ‘እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አል​ተ​ገ​ለ​ጠ​ል​ህም’ ቢሉኝ ምን እላ​ቸ​ዋ​ለሁ?” አለ።


ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት፥ “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አል​ሰ​ሙ​ኝም፤ እን​ዴ​ትስ ፈር​ዖን ይሰ​ማ​ኛል? እኔም አን​ደ​በተ ርቱዕ አይ​ደ​ለ​ሁም” ብሎ ተና​ገረ።


ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት፥ “እነሆ፥ እኔ አን​ደ​በተ ርቱዕ አይ​ደ​ለ​ሁም፤ እን​ዴ​ትስ ፈር​ዖን ይሰ​ማ​ኛል?” አለ።


እኔም፥ “ከን​ፈ​ሮች የረ​ከ​ሱ​ብኝ ሰው በመ​ሆኔ፥ ከን​ፈ​ሮ​ቻ​ቸው በረ​ከ​ሱ​ባ​ቸው ሕዝብ መካ​ከል በመ​ቀ​መጤ ዐይ​ኖች የሠ​ራ​ዊ​ትን ጌታ ንጉ​ሡን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ አዩ ጠፍ​ቻ​ለ​ሁና ወዮ​ልኝ!” አልሁ።


እኔም፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! ወዮ! እነሆ ነቢ​ያት፦ እው​ነ​ት​ንና ሰላ​ምን በዚህ ስፍራ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ እንጂ ሰይ​ፍን አታ​ዩም፤ ራብም አያ​ገ​ኛ​ች​ሁም ይሉ​አ​ቸ​ዋል” አልሁ።


“ወዮ! አቤቱ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! እነሆ አንተ ሰማ​ይ​ንና ምድ​ርን በታ​ላቅ ኀይ​ል​ህና በተ​ዘ​ረ​ጋች ክን​ድህ ፈጥ​ረ​ሃል፤ ከአ​ን​ተም የሚ​ሳን ምንም ነገር የለም።


ነቢዩ ኤር​ም​ያ​ስም ይህን ቃል ሁሉ ለይ​ሁዳ ንጉሥ ለሴ​ዴ​ቅ​ያስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ነገ​ረው።


እኔም፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ወዮ! አንተ ሰይፍ እስከ ሰው​ነ​ታ​ቸው ድረስ እስ​ክ​ት​ደ​ርስ ሰላም ይሆ​ን​ላ​ች​ኋል” ብለህ ይህን ሕዝ​ብና ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እጅግ አታ​ለ​ልህ አልሁ።


እኔም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! ይህ አግ​ባብ አይ​ደ​ለም፤ እነሆ ሰው​ነቴ አል​ረ​ከ​ሰ​ችም፤ ከታ​ና​ሽ​ነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ጥን​ብና አውሬ የሰ​በ​ረ​ውን ከቶ አል​በ​ላ​ሁም፤ ርኵ​ስም ሥጋ በአፌ ውስጥ አል​ገ​ባም” አልሁ።


ሩጥ፥ ይህንም ጕልማሳ እንዲህ በለው፦ ኢየሩሳሌም በውስጥዋ ካሉት ሰዎችና እንስሶች ብዛት የተነሣ ቅጥር እንደሌላቸው መንደሮች ሆና ትኖራለች።