ኤርምያስ 14:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 እኔም፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ወዮ! እነሆ ነቢያት፦ እውነትንና ሰላምን በዚህ ስፍራ እሰጣችኋለሁ እንጂ ሰይፍን አታዩም፤ ራብም አያገኛችሁም ይሉአቸዋል” አልሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 እኔም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ወዮ! ነቢያቱ ‘ሰይፍ አታዩም፤ ራብም አያገኛችሁም፤ ነገር ግን በዚህ ስፍራ ዘለቄታ ያለው እውነተኛ ሰላም እሰጣችኋለሁ’ ይላል ይሏቸዋል” አልሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 እኔም፦ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ወዮ! እነሆ፥ ነቢያት፦ ‘ዘላቂ ሰላም በዚህ ስፍራ እሰጣችኋለሁ እንጂ ሰይፍን አታዩም፥ ራብም አያገኛችሁም’ ይሉአቸዋል” አልሁ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ነቢያቱ ‘ጦርነት ሆነ ራብ አይኖርም’ እያሉ ለሕዝቡ ይናገራሉ፤ ‘በምድራችን ዘላቂ ሰላም ብቻ እንደሚሰፍን እግዚአብሔር ተናግሮአል’ ይላሉ።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 እኔም፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! እነሆ፥ ነቢያት፦ በእውነት ሰላምን በዚህ ስፍራ እሰጣችኋለሁ እንጂ ሰይፍን አታዩም፥ ራብም አያገኛችሁም ይሉአቸዋል አልሁ። ምዕራፉን ተመልከት |