የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 27:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ዲ​ህም ሆነ፦ ይስ​ሐቅ ፈጽሞ ከአ​ረጀ በኋላ ዐይ​ኖቹ ፈዝ​ዘው አያ​ይም ነበር። ታላ​ቁን ልጁን ዔሳ​ው​ንም ጠርቶ፥ “ልጄ ሆይ፥” አለው፤ እር​ሱም፥ “እነሆ አለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይሥሐቅ አርጅቶ፣ ዐይኖቹ ደክመው ማየት በተሳናቸው ጊዜ፣ ታላቁን ልጁን ዔሳውን ጠርቶ፣ “ልጄ ሆይ” አለው። እርሱም፣ “እነሆ፤ አለሁ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲህም ሆነ፥ ይስሐቅ ሸምግሎ ዐይኖቹ ከማየት በፈዘዙ ጊዜ ታላቁን ልጁን ዔሳውን ጠርቶ፥ “ልጄ ሆይ፥” አለው እርሱ፥ “እነሆ አለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይስሐቅ አርጅቶ ዐይኖቹም ፈዘው ነበር፤ ታላቁን ልጁን ዔሳውን “ልጄ ሆይ!” ብሎ ጠራው፤ ልጁም “እነሆ፥ አለሁ!” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይስሐቅ ሸምግሎ ዓይኖቹ ከማየት በፈዘዙ ጊዜ ታላቁን ልጁን ዔሳውን ጠርቶ፦ ልጄ ሆይ አለው እርሱም፦ እነሆ አለሁ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 27:1
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያዕ​ቆ​ብም፥ “ብኵ​ር​ና​ህን ትሰ​ጠኝ ዘንድ እስኪ ዛሬ ማል​ልኝ” አለው። ዔሳ​ውም ማለ​ለት፤ ብኵ​ር​ና​ው​ንም ለያ​ዕ​ቆብ ሸጠ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዐይ​ኖች ከሽ​ም​ግ​ልና የተ​ነሣ ከብ​ደው ነበር፤ ማየ​ትም አይ​ች​ልም ነበር፤ ወደ እር​ሱም አቀ​ረ​ባ​ቸው፤ ሳማ​ቸ​ውም፤ አቀ​ፋ​ቸ​ውም።


የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምም ሚስት እን​ዲሁ አደ​ረ​ገች፤ ተነ​ሥ​ታም እን​ጀራ፥ የወ​ይን ዘለ​ላና አንድ ማሠሮ ማር በመ​ያዝ ወደ ሴሎ ሄደች፤ ወደ አኪ​ያም ቤት ገባች። አኪያ ግን ስለ መሸ​ም​ገሉ ዐይ​ኖቹ ፈዝ​ዘው ነበ​ርና ማየት አል​ቻ​ለም።


ቤት ጠባ​ቆች በሚ​ን​ቀ​ጠ​ቀ​ጡ​በት፥ ኀያ​ላን ሰዎ​ችም በሚ​ጐ​ብ​ጡ​በት፥ ጥቂ​ቶች ሆነ​ዋ​ልና ፈጭ​ታ​ዎች ሥራ በሚ​ፈ​ቱ​በት፥ በመ​ስ​ኮ​ትም ሆነው የሚ​መ​ለ​ከቱ በሚ​ጨ​ል​ሙ​በት፥


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ሊገ​ለ​ጥ​በት ነው እንጂ እርሱ አል​በ​ደ​ለም፤ ወላ​ጆ​ቹም አል​በ​ደ​ሉም።


ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድ​ሜዉ መቶ ሃያ ዓመት ነበረ፤ ዐይ​ኖ​ቹም አል​ፈ​ዘ​ዙም፤ ጕል​በ​ቱም አል​ደ​ከ​መም ነበር።


በዚ​ያም ዘመን እን​ዲህ ሆነ፤ ዔሊም በስ​ፍ​ራው ተኝቶ ሳለ፥ ዐይ​ኖቹ መፍ​ዘዝ ጀም​ረው ነበር። ማየ​ትም አይ​ች​ልም ነበር።