Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 48:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዐይ​ኖች ከሽ​ም​ግ​ልና የተ​ነሣ ከብ​ደው ነበር፤ ማየ​ትም አይ​ች​ልም ነበር፤ ወደ እር​ሱም አቀ​ረ​ባ​ቸው፤ ሳማ​ቸ​ውም፤ አቀ​ፋ​ቸ​ውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በዚህ ጊዜ እስራኤል ዐይኖቹ በእርጅና ምክንያት በመድከማቸው አጥርቶ ማየት ይሳነው ነበር፤ ስለዚህ ዮሴፍ ልጆቹን አባቱ ዘንድ አቀረባቸው፤ አባቱም ስሞ ዐቀፋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የእስራኤልም ዐይኖች ከሽምግልና የተነሣ ደክመው ነበር፥ ማየትም አይችልም ነበር፥ ወደ እርሱም አቀረባቸው፥ ሳማቸውም፥ አቀፋቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 የያዕቆብ ዐይኖች በእርጅናው ምክንያት ስለ ደከሙ አጥርቶ ማየት አይችልም ነበር፤ ስለዚህ ዮሴፍ ልጆቹን ወደ እርሱ አቀረበለት፤ እርሱም ዕቅፍ አድርጎ ሳማቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የእስራኤልም ዓይኖች ከሸምግልና የተነሣ ከብደው ነበር። ማየትም አይችልም ነበር ወደ እርሱም አቀረባቸው ሳማቸውም አቀፋቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 48:10
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወደ እር​ሱም ቀረበ፤ ሳመ​ውም፤ የል​ብ​ሱ​ንም ሽታ አሸ​ተተ፤ ባረ​ከ​ውም፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “የልጄ ሽታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ባረ​ከው የእ​ርሻ ሽታ ነው፤


እን​ዲ​ህም ሆነ፦ ይስ​ሐቅ ፈጽሞ ከአ​ረጀ በኋላ ዐይ​ኖቹ ፈዝ​ዘው አያ​ይም ነበር። ታላ​ቁን ልጁን ዔሳ​ው​ንም ጠርቶ፥ “ልጄ ሆይ፥” አለው፤ እር​ሱም፥ “እነሆ አለሁ” አለው።


በውኑ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ማዳን አት​ች​ል​ምን? ጆሮ​ውስ አይ​ሰ​ማ​ምን?


እነ​ዚህ ሕዝ​ቦች በዐ​ይ​ና​ቸው እን​ዳ​ያዩ፥ በጆ​ሮ​አ​ቸ​ውም እን​ዳ​ይ​ሰሙ፥ በል​ባ​ቸ​ውም እን​ዳ​ያ​ስ​ተ​ውሉ ተመ​ል​ሰ​ውም እን​ዳ​ል​ፈ​ው​ሳ​ቸው፥ ልባ​ቸ​ውን አደ​ን​ድ​ነ​ዋ​ልና፥ ጆሮ​አ​ቸ​ው​ንም ደፍ​ነ​ዋ​ልና፥ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም ጨፍ​ነ​ዋ​ልና።


ኤል​ሳ​ዕም በሬ​ዎ​ቹን ተወ፤ ኤል​ያ​ስ​ንም ተከ​ትሎ ሄደ፥ “አባ​ቴ​ንና እና​ቴን እስ​ማ​ቸው ዘንድ፥ እባ​ክህ ተወኝ፤ ከዚ​ያም በኋላ እከ​ተ​ል​ሃ​ለሁ” አለው። እር​ሱም“ሂድና ተመ​ለስ፤ ምን አድ​ር​ጌ​ል​ሃ​ለሁ?” አለው።


ዔሊም የዘ​ጠና ስም​ንት ዓመት ሽማ​ግሌ ነበረ፤ ዐይ​ኖ​ቹም ፈዝ​ዘው አያ​ይም ነበር።


በዚ​ያም ዘመን እን​ዲህ ሆነ፤ ዔሊም በስ​ፍ​ራው ተኝቶ ሳለ፥ ዐይ​ኖቹ መፍ​ዘዝ ጀም​ረው ነበር። ማየ​ትም አይ​ች​ልም ነበር።


ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ ሳማ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ አለ​ቀሰ፤ ከዚ​ያም በኋላ ወን​ድ​ሞቹ ከእ​ርሱ ጋር ተጨ​ዋ​ወቱ።


ላባም ማልዶ ተነ​ሥቶ ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ችን ልጆ​ቹን ሳመ፤ ባረ​ካ​ቸ​ውም፤ ላባም ተመ​ልሶ ወደ ስፍ​ራው ሄደ።


እስ​ራ​ኤ​ልም የዮ​ሴ​ፍን ልጆች ለይቶ፥ “እነ​ዚህ ምኖ​ችህ ናቸው?” አለው።


እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “ከፊ​ትህ አል​ተ​ለ​የ​ሁም፤ እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘር​ህን ደግሞ አሳ​የኝ” አለው።


ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድ​ሜዉ መቶ ሃያ ዓመት ነበረ፤ ዐይ​ኖ​ቹም አል​ፈ​ዘ​ዙም፤ ጕል​በ​ቱም አል​ደ​ከ​መም ነበር።


ቤት ጠባ​ቆች በሚ​ን​ቀ​ጠ​ቀ​ጡ​በት፥ ኀያ​ላን ሰዎ​ችም በሚ​ጐ​ብ​ጡ​በት፥ ጥቂ​ቶች ሆነ​ዋ​ልና ፈጭ​ታ​ዎች ሥራ በሚ​ፈ​ቱ​በት፥ በመ​ስ​ኮ​ትም ሆነው የሚ​መ​ለ​ከቱ በሚ​ጨ​ል​ሙ​በት፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች