Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 27:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ይስሐቅ አርጅቶ ዐይኖቹም ፈዘው ነበር፤ ታላቁን ልጁን ዔሳውን “ልጄ ሆይ!” ብሎ ጠራው፤ ልጁም “እነሆ፥ አለሁ!” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ይሥሐቅ አርጅቶ፣ ዐይኖቹ ደክመው ማየት በተሳናቸው ጊዜ፣ ታላቁን ልጁን ዔሳውን ጠርቶ፣ “ልጄ ሆይ” አለው። እርሱም፣ “እነሆ፤ አለሁ” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እንዲህም ሆነ፥ ይስሐቅ ሸምግሎ ዐይኖቹ ከማየት በፈዘዙ ጊዜ ታላቁን ልጁን ዔሳውን ጠርቶ፥ “ልጄ ሆይ፥” አለው እርሱ፥ “እነሆ አለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እን​ዲ​ህም ሆነ፦ ይስ​ሐቅ ፈጽሞ ከአ​ረጀ በኋላ ዐይ​ኖቹ ፈዝ​ዘው አያ​ይም ነበር። ታላ​ቁን ልጁን ዔሳ​ው​ንም ጠርቶ፥ “ልጄ ሆይ፥” አለው፤ እር​ሱም፥ “እነሆ አለሁ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ይስሐቅ ሸምግሎ ዓይኖቹ ከማየት በፈዘዙ ጊዜ ታላቁን ልጁን ዔሳውን ጠርቶ፦ ልጄ ሆይ አለው እርሱም፦ እነሆ አለሁ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 27:1
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያዕቆብም “እንግዲያውስ ብኲርናህን እንደምትሸጥልኝ መጀመሪያ ማልልኝ” አለው። ስለዚህ ዔሳው ምሎ ብኲርናውን ለያዕቆብ ሸጠ።


የያዕቆብ ዐይኖች በእርጅናው ምክንያት ስለ ደከሙ አጥርቶ ማየት አይችልም ነበር፤ ስለዚህ ዮሴፍ ልጆቹን ወደ እርሱ አቀረበለት፤ እርሱም ዕቅፍ አድርጎ ሳማቸው።


ስለዚህ የኢዮርብዓም ሚስት ይህን ሁሉ አዘጋጅታ በሴሎ ወደሚገኘው ወደ አኪያ ቤት ሄደች፤ ነቢዩ አኪያም በዕድሜው ከመሸምገሉ የተነሣ ዐይኖቹ ፈዘው ነበር፤


የምትተማመንባቸው ክንዶችህ ይንቀጠቀጣሉ፤ አሁን ብርቱ የሆኑ እግሮችህ ይዝላሉ፤ ጥርሶችህ ቊጥራቸው ከማነሳቸው የተነሣ ምግብ ማኘክ አይችሉም፤ ዐይኖችህ ከመፍዘዛቸው የተነሣ አጥርተው ማየት ይሳናቸዋል።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ይህ ሰው ዕውር ሆኖ የተወለደው በእርሱ ወይም በወላጆቹ ኃጢአት ምክንያት አይደለም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው።


ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ኻያ ዓመት ነበር፤ ነገር ግን ዐይኑ ያልፈዘዘና ጒልበቱም ያልደከመ ገና ብርቱ ሰው ነበር።


በእርጅና ምክንያት ዐይኖቹ ፈዘው የነበሩት ዔሊ ከዕለታት በአንደኛው ቀን ሌሊት በመኝታ ክፍሉ ተኝቶ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች