የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 2:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሜዳ ቍጥ​ቋጦ ሁሉ በም​ድር ላይ ከመ​ኖሩ በፊት፥ የሜ​ዳ​ውም ቡቃያ ሁሉ ከመ​ብ​ቀሉ በፊት፥ አዳ​ምም ከመ​ፈ​ጠሩ በፊት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ በም​ድር ላይ አላ​ዘ​ነ​በም ነበር፤ ምድ​ር​ንም የሚ​ሠ​ራ​ባት ሰው አል​ነ​በ​ረም።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሜዳ ቡቃያ ገና በምድር ላይ አልታየም፤ የሜዳ ተክልም ገና አልበቀለም፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር አምላክ በመሬት ላይ ገና ዝናብ አላዘነበም ነበር፤ ምድርንም የሚያለማ ሰው አልነበረም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የሜዳ ቁጥቋጦ ሁሉ በምድር ላይ ከመኖሩ በፊት፥ የሜዳውም ቡቃያ ሁሉ ከመብቀሉ በፊት፥ ጌታ እግዚአብሔር በምድር ላይ አላዘነበም ነበር፤ ምድርንም የሚሠራባት ሰው አልነበረም።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዝናብን ባለማዝነቡና ምድርንም የሚያለማ ሰው ባለመኖሩ፥ በምድር ላይ ምንም ዐይነት ተክል አልነበረም፤ ምንም ዐይነት ቡቃያ አልበቀለም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሜዳ ቁጥቋጦ ሁሉ በምድር ላይ ገና አልነበረም የሜዳውም ቡቃያ ሁሉ ገና አልነበረም ነበር፤ እግዚአብሔር አምላክ ምድር ላይ አላዘነበም ነበርና፤ ምድርም የሚሠራባት በምድር ላይ አላዘነበም ነበርና፤

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 2:5
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን የውኃ ምንጭ ከም​ድር ይወጣ ነበር፤ የም​ድ​ር​ንም ፊት ሁሉ ያጠጣ ነበር።


ስለ​ዚህ የተ​ገ​ኘ​ባ​ትን መሬት ያርስ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ደስታ ከሚ​ገ​ኝ​ባት ገነት አስ​ወ​ጣው።


ምድ​ር​ንም ባረ​ስህ ጊዜ እን​ግ​ዲህ ኀይ​ል​ዋን አት​ሰ​ጥ​ህም፤ በም​ድር ላይ ኮብ​ላ​ይና ተቅ​በ​ዝ​ባዥ ትሆ​ና​ለህ።”


እር​ስ​ዋም “ወንድ ልጅ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ኘሁ” አለች። ደግ​ሞም ወን​ድ​ሙን አቤ​ልን ወለ​ደ​ችው። አቤ​ልም በግ ጠባቂ ሆነ፤ ቃየ​ልም ምድ​ርን የሚ​ያ​ርስ ሆነ።


በም​ድር ላይ ዝና​ብን ይሰ​ጣል፥ ከሰ​ማ​ይም በታች ውኃን ይል​ካል።


ሰው ግፍ ያደ​ር​ግ​ባ​ቸው ዘንድ አል​ተ​ወም፥ ስለ እነ​ር​ሱም ነገ​ሥ​ታ​ቱን ገሠጸ።


ብቻ​ውን ታላ​ላቅ ብር​ሃ​ና​ትን የሠራ፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


ምድ​ርን በኀ​ይሉ የፈ​ጠረ፥ ዓለ​ሙን በጥ​በቡ ያጸና፥ ሰማ​ያ​ት​ንም በማ​ስ​ተ​ዋሉ የዘ​ረጋ እርሱ ነው።


በላይ በሰ​ማይ ውኆ​ችን ይሰ​በ​ስ​ባል፤ ከም​ድ​ርም ዳርቻ ደመ​ና​ትን ከፍ ያደ​ር​ጋል፤ ለዝ​ና​ብም መብ​ረ​ቅን ያደ​ር​ጋል፤ ነፋ​ስ​ንም ከቤተ መዛ​ግ​ብቱ ያወ​ጣል።


በውኑ በአ​ሕ​ዛብ ጣዖ​ታት መካ​ከል ያዘ​ንብ ዘንድ የሚ​ችል ይገ​ኛ​ልን? ወይስ ሰማይ ዝናብ ሊሰ​ጥና ሊያ​ጠ​ግብ ይች​ላ​ልን? አቤቱ አም​ላ​ካ​ችን ሆይ አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? አንተ ይህን ነገር ሁሉ አድ​ር​ገ​ሃ​ልና ስለ​ዚህ አን​ተን በተ​ስፋ እን​ጠ​ባ​በ​ቃ​ለን።


ምድ​ርም በእ​ር​ስዋ የሚ​ወ​ር​ደ​ውን ዝናም ከጠ​ጣች፥ ያን​ጊዜ ስለ እርሱ ያረ​ሱ​ላ​ትን መላ​ካም ቡቃያ ታበ​ቅ​ላ​ለች፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘን​ድም በረ​ከ​ትን ታገ​ኛ​ለች።