የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤፌሶን 3:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስለ እና​ንተ የሰ​ጠ​ኝን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የጸ​ጋ​ውን ስጦታ ሰም​ታ​ች​ኋል።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለ እናንተ ስለ ተሰጠኝ የእግዚአብሔር ጸጋ መጋቢነት በርግጥ ሰምታችኋል፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በእርግጥ ስለ እናንተ ሲባል ስለ ተሰጠኝ ስለ እግዚአብሔር ጸጋ መጋቢነት ሰምታችኋል፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለእናንተ ጥቅም እንዳውለው እግዚአብሔር በጸጋው የአገልግሎት ዕድል እንደ ሰጠኝ በእርግጥ ሰምታችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለእናንተ ስለ ተሰጠኝ ስለ እግዚአብሔር ጸጋ መጋቢነት በእርግጥ ሰምታችኋል፤

ምዕራፉን ተመልከት



ኤፌሶን 3:2
27 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ሲሠሩ፥ ሲጾ​ሙም መን​ፈስ ቅዱስ፥ “በር​ና​ባ​ስ​ንና ሳው​ልን እኔ ለፈ​ለ​ግ​ኋ​ቸው ሥራ ለዩ​ልኝ” አላ​ቸው።


ጳው​ሎ​ስና በር​ና​ባ​ስም ደፍ​ረው እን​ዲህ ብለው ተና​ገ​ሩ​አ​ቸው፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ለእ​ና​ንተ አስ​ቀ​ድሞ ልን​ነ​ግ​ራ​ችሁ ይገ​ባል፤ እንቢ ብት​ሉና ራሳ​ች​ሁን ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት የተ​ዘ​ጋጀ ባታ​ደ​ርጉ ግን እነሆ፥ ወደ አሕ​ዛብ እን​መ​ለ​ሳ​ለን።


እር​ሱም፦ ‘ሂድ ርቀው ወደ አሉ አሕ​ዛብ እል​ክ​ሃ​ለ​ሁና’ ” አለኝ።


ጌታ​ች​ንም እን​ዲህ አለው፥ “ተነ​ሥና ሂድ፤ በአ​ሕ​ዛ​ብና በነ​ገ​ሥ​ታት፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም ፊት ስሜን ይሸ​ከም ዘንድ ለእኔ የተ​መ​ረጠ ዕቃ አድ​ር​ጌ​ዋ​ለ​ሁና።


በስሙ እን​ዲ​ያ​ምኑ አሕ​ዛ​ብን ልና​ስ​ተ​ምር ሐዋ​ር​ያት ተብ​ለን የተ​ሾ​ም​ን​በ​ትና ጸጋን ያገ​ኘ​ን​በት፥


ለእ​ና​ንተ ለአ​ሕ​ዛብ እና​ገ​ራ​ለሁ፤ እኔ ለአ​ሕ​ዛብ ሐዋ​ር​ያ​ቸው እንደ መሆኔ መጠን መል​እ​ክ​ቴን አከ​ብ​ራ​ታ​ለሁ።


በተ​ሰ​ጠኝ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸጋ ሁላ​ች​ሁም እን​ዳ​ት​ታ​በዩ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ ራሳ​ች​ሁን ከዝ​ሙት የም​ታ​ነ​ጹ​በ​ትን ዐስቡ እንጂ ትዕ​ቢ​ትን አታ​ስቡ፤ ሁሉም እንደ እም​ነቱ መጠን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አደ​ለው ይኑር።


እኛ የክ​ር​ስ​ቶስ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ሥ​ጢሩ መጋ​ቢ​ዎች እንደ ሆን ሰው ስለ እኛ እን​ዲህ ያስብ።


በአ​ይ​ሁድ ሥር​ዐት ውስጥ በነ​በ​ርሁ ጊዜ፥ የነ​በ​ረ​ውን የቀ​ድሞ ሥራ​ዬን ሰም​ታ​ች​ኋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን እጅግ አሳ​ድ​ድና መከራ አጸ​ና​ባ​ቸው ነበር።


የሚ​ደ​ር​ስ​በ​ት​ንም ጊዜ​ውን ወሰነ፤ በሰ​ማ​ይና በም​ድር ያለ​ውም ሁሉ ይታ​ደስ ዘንድ ክር​ስ​ቶ​ስን በሁሉ ላይ አላ​ቀው።


በኀ​ይሉ አጋ​ዥ​ነት እንደ ሰጠኝ እንደ ጸጋው ስጦታ መጠን እኔ መል​እ​ክ​ተ​ኛና አዋጅ ነጋሪ የሆ​ን​ሁ​ለት፥


ከቅ​ዱ​ሳን ሁሉ ለማ​ንስ ለእኔ የማ​ይ​መ​ረ​መ​ረ​ውን የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ባለ​ጸ​ግ​ነት ለአ​ሕ​ዛብ አስ​ተ​ምር ዘንድ ይህን ጸጋ ሰጠኝ።


ሁሉን በፈ​ጠረ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዘ​ለ​ዓ​ለም የተ​ሰ​ወረ የዚህ ምሥ​ጢር ሥር​ዐ​ት​ንም ለሁሉ እገ​ልጥ ዘንድ፤


በር​ግጥ ከሰ​ማ​ች​ሁት፥ እው​ነት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነውና እው​ነ​ትን በእ​ርሱ ዘንድ ትማ​ራ​ላ​ችሁ፤


ከእኛ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ በክ​ር​ስ​ቶስ ስጦታ መጠን ጸጋው ተሰ​ጥ​ቶ​ናል።


በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ማመ​ና​ች​ሁ​ንና ቅዱ​ሳ​ን​ንም ሁሉ መው​ደ​ዳ​ች​ሁን ከሰ​ማ​ን​በት ጊዜ ጀምሮ፥ ስለ እና​ንተ እን​ጸ​ል​ያ​ለን።


ይህም ወደ እና​ንተ የደ​ረ​ሰ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጸጋ በእ​ው​ነት ከሰ​ማ​ች​ሁ​በ​ትና ከአ​ያ​ች​ሁ​በት ቀን ጀምሮ በመ​ላው ዓለም ያድ​ግና ያፈራ ዘንድ ነው።


እኔም ለዚህ ነገር አዋጅ ነጋሪና ሐዋርያ በእምነትና በእውነትም የአሕዛብ አስተማሪ ለመሆን ተሾምሁ፤ እውነት እናገራለሁ፤ አልዋሽም።