Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤፌሶን 4:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በር​ግጥ ከሰ​ማ​ች​ሁት፥ እው​ነት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነውና እው​ነ​ትን በእ​ርሱ ዘንድ ትማ​ራ​ላ​ችሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በርግጥ ስለ እርሱ ሰምታችኋል፤ በኢየሱስም እንዳለው እውነት በርሱ ተምራችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በእርግጥ ሰምታችሁታልና፤ እውነትም በኢየሱስ እንዳለ በእርሱ ተምራችኋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 በእርግጥ ስለ እርሱ ሰምታችኋል፤ በኢየሱስ ባለው እውነት መሠረትም ከእርሱ ተምራችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በእርግጥ ሰምታችሁታልና፥ እውነትም በኢየሱስ እንዳለ በእርሱ ተምራችኋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤፌሶን 4:21
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፈሳሽ ወንዝ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከተማ ደስ ያሰ​ኛል፤ ልዑል ማደ​ሪ​ያ​ውን ቀደሰ።


እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆም፥ ከደመናው “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት፤” የሚል ድምፅ መጣ።


“እና​ን​ተን የሚ​ሰማ እኔን ይሰ​ማል፤ እና​ን​ተ​ንም እንቢ የሚል እኔን እንቢ ይላል፤ እኔ​ንም እንቢ የሚል የላ​ከ​ኝን እንቢ ይላል፤ እኔ​ንም የሚ​ሰማ የላ​ከ​ኝን ይሰ​ማል።”


ኦሪት በሙሴ ተሰ​ጥ​ታን ነበ​ርና፤ ጸጋና እው​ነት ግን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሆነ​ልን።


የእኔ የሆኑ በጎች ግን ቃሌን ይሰ​ሙ​ኛል፤ እኔም አው​ቃ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይከ​ተ​ሉ​ኛል።


እር​ሱም ዓለም ስለ​ማ​ያ​የ​ውና ስለ​ማ​ያ​ው​ቀው ሊቀ​በ​ለው የማ​ይ​ቻ​ለው የእ​ው​ነት መን​ፈስ ነው፤ እና​ንተ ግን ታው​ቁ​ታ​ላ​ችሁ፤ በእ​ና​ንተ ዘንድ ይኖ​ራ​ልና፤ ያድ​ር​ባ​ች​ሁ​ማ​ልና።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “የእ​ው​ነ​ትና የሕ​ይ​ወት መን​ገድ እኔ ነኝ፤ በእኔ በኩል ካል​ሆነ በቀር ወደ አብ የሚ​መጣ የለም።


ነገር ግን ያላ​መ​ኑ​በ​ትን እን​ዴት ይጠ​ሩ​ታል? ባል​ሰ​ሙ​ትስ እን​ዴት ያም​ናሉ? ያለ ሰባ​ኪስ እን​ዴት ይሰ​ማሉ?


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠው ተስፋ ሁሉ በክ​ር​ስ​ቶስ እው​ነት ሆኖ​አ​ልና፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ርሱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር አሜን እን​ላ​ለን።


የክ​ር​ስ​ቶስ ዕው​ነት አብ​ሮኝ ይኖ​ራ​ልና፥ ይህቺ ደስ​ታዬ በአ​ካ​ይያ አው​ራጃ አል​ተ​ከ​ለ​ከ​ለ​ች​ብ​ኝም።


እና​ን​ተም ልት​ድ​ኑ​በት የተ​ማ​ራ​ች​ሁ​ትን የእ​ው​ነት ቃል ሰም​ታ​ች​ሁና አም​ና​ችሁ፤ ተስፋ ባደ​ረ​ገ​ላ​ችሁ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ታተ​ማ​ችሁ።


መጥ​ቶም፤ ቀር​በን ለነ​በ​ር​ነው ሰላ​ምን፥ ርቃ​ችሁ ለነ​በ​ራ​ች​ሁት ለእ​ና​ን​ተም ሰላ​ምን ሰጠን።


የእ​ው​ነት ቃል በሆ​ነው በወ​ን​ጌል ትም​ህ​ርት፥ አስ​ቀ​ድሞ ስለ ሰማ​ች​ሁት፥ በሰ​ማይ ስለ ተዘ​ጋ​ጀ​ላ​ችሁ ተስ​ፋ​ች​ሁም እን​ጸ​ል​ያ​ለን።


ይህም ወደ እና​ንተ የደ​ረ​ሰ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጸጋ በእ​ው​ነት ከሰ​ማ​ች​ሁ​በ​ትና ከአ​ያ​ች​ሁ​በት ቀን ጀምሮ በመ​ላው ዓለም ያድ​ግና ያፈራ ዘንድ ነው።


በእ​ርሱ ተመ​ሥ​ር​ታ​ችሁ ታነጹ፤ በም​ስ​ጋ​ናው ትበዙ ዘንድ፥ በተ​ማ​ራ​ች​ሁት ሃይ​ማ​ኖት ጽኑ።


የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች