2 ሳሙኤል 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሳኦልም ልጅ ለኢያቡስቴ የጭፍራ አለቆች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ የአንደኛው ስም በዓና፥ የሁለተኛውም ስም ሬካብ ነበረ፤ ከብንያምም ልጆች የቤሮታዊው የሬሞን ልጆች ነበሩ፤ ቤሮትም ለብንያም ተቈጥራ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ የወራሪ ጭፍራ ቡድን መሪዎች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ አንዱ በዓና ሌላው ደግሞ ሬካብ ይባሉ ነበር። እነርሱም ከብንያም ነገድ የብኤሮት ተወላጅ የሆነው የሬሞን ልጆች ነበሩ፤ ብኤሮት ከብንያም ክፍል እንደ አንዱ ትቈጠራለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ የሳኦል ልጅ ኢያቡስቴ የወራሪ ጭፍራ ቡድን መሪዎች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፤ አንዱ በዓና ሌላው ደግሞ ሬካብ ይባሉ ነበር። እነርሱም የበኤሮት ተወላጅ የሆነው የሬሞን ልጆች የነበሩ ሲሆን፥ በኤሮትም ከብንያም ክፍል እንደ አንዱ ተቆጥራ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያቡስቴ የወራሪ ጭፍራ ቡድን መሪዎች የሆኑ ሁለት መኰንኖች ነበሩት፤ እነርሱም ከብንያም ነገድ የበኤሮት ተወላጆች የሆኑት የሪሞን ልጆች በዓናና ሬካብ ነበሩ፤ በኤሮት የብንያም ክፍል እንደ ሆነች ይታሰብ ነበር፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሳኦልም ልጅ ለኢያቡስቴ የጭፍራ አለቆች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩት፥ የአንዱም ስም በዓና፥ የሁለተኛውም ስም ሬካብ ነበረ፥ ከብንያምም ልጆች የብኤሮታዊው የሬሞን ልጆች ነበሩ፥ ብኤሮትም ለብንያም ተቆጥራ ነበር። |
በዚያ ጊዜም የዳዊት ብላቴኖችና ኢዮአብ ከዘመቻ ታላቅ ምርኮ ይዘው መጡ። አበኔር ግን ዳዊት አሰናብቶት በደኅና ሄዶ ነበር እንጂ በኬብሮን አልነበረም።
የቤሮታዊውም የሬሞን ልጆች ሬካብና በዓና ቀኑ ሲሞቅ ወደ ኢያቡስቴ ቤት መጡ፤ እርሱም በቀትር ጊዜ በአልጋው ላይ ተኝቶ ነበር።
ዳዊትም ለቤሮታዊው ለሬሞን ልጆች ለሬካብና ለወንድሙ ለበዓና እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፥ “ነፍሴን ከመከራ ሁሉ ያዳነ ሕያው እግዚአብሔርን!
ብዙም መብል አዘጋጀላቸው፤ በበሉና በጠጡ ጊዜም አሰናበታቸው፤ እነርሱም ወደ ጌታቸው ሄዱ። ከዚያም በኋላ የሶርያውያን አደጋ ጣዮች ዳግመኛ ወደ እስራኤል ሀገር አልመጡም።
የእስራኤልም ልጆች ተጕዘው በሦስተኛው ቀን ወደ ከተሞቻቸው ደረሱ፤ ከተሞቻቸውም ገባዖን፥ ከፊራ፥ ብኤሮትና ኢያሪም ነበሩ።