Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ነገሥት 6:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ብዙም መብል አዘ​ጋ​ጀ​ላ​ቸው፤ በበ​ሉና በጠጡ ጊዜም አሰ​ና​በ​ታ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ወደ ጌታ​ቸው ሄዱ። ከዚ​ያም በኋላ የሶ​ር​ያ​ው​ያን አደጋ ጣዮች ዳግ​መኛ ወደ እስ​ራ​ኤል ሀገር አል​መ​ጡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ስለዚህ ታላቅ ግብዣ አዘጋጅቶላቸው ከበሉና ከጠጡ በኋላ አሰናብቷቸው ወደ ጌታቸው ሄዱ። የሶርያ አደጋ ጣዮችም የእስራኤልን ምድር ለመውረር ከዚያ በኋላ አልተመለሱም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ስለዚህም የእስራኤል ንጉሥ ለእነርሱ ታላቅ ግብዣ አደረገላቸው፤ ከበሉና ከጠጡም በኋላ ወደ ሶርያ ንጉሥ መልሶ ላካቸው፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ሶርያውያን በእስራኤል ምድር ላይ ወረራ ማድረጋቸውን አቆሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ስለዚህም የእስራኤል ንጉሥ ለእነርሱ ታላቅ ግብዣ አደረገላቸው፤ ከበሉና ከጠጡም በኋላ ወደ ሶርያ ንጉሥ መልሶ ላካቸው፤ ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ሶርያውያን በእስራኤል ምድር ላይ ወረራ ማድረጋቸውን አቆሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ብዙም መብል አዘጋጀላቸው፤ በበሉና በጠጡ ጊዜም አሰናበታቸው፤ እነርሱም ወደ ጌታቸው ሄዱ። ከዚያም በኋላ የሶርያ አደጋ ጣዮች ወደ እስራኤል አገር አልመጡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ነገሥት 6:23
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንም ጋር ወደ ሰልፍ በወጣ ጊዜ ከእ​ስ​ራ​ኤል ምድር ታናሽ ብላ​ቴና ሴት ማረከ፤ ለሚ​ስ​ቱም አገ​ል​ጋይ አደ​ረ​ጋት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንን አደጋ ጣዮች፥ የሶ​ር​ያ​ው​ያ​ን​ንም አደጋ ጣዮች፥ የሞ​ዓ​ባ​ው​ያ​ን​ንም አደጋ ጣዮች፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች አደጋ ጣዮች ሰደ​ደ​በት፤ በባ​ሪ​ያ​ዎቹ በነ​ቢ​ያት ቃል እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ያጠ​ፉት ዘንድ በይ​ሁዳ ላይ ሰደ​ዳ​ቸው።


አሁ​ንም ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ውደዱ፤ መል​ካ​ምም አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ እን​ዲ​መ​ል​ሱ​ላ​ችሁ ተስፋ ሳታ​ደ​ርጉ አበ​ድሩ፤ ዋጋ​ች​ሁም ብዙ ይሆ​ናል፤ የል​ዑ​ልም ልጆች ትሆ​ና​ላ​ችሁ፤ እርሱ ለበ​ጎ​ዎ​ችና ለክ​ፉ​ዎች ቸር ነውና።


ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅ ብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን?


በስ​ማ​ቸ​ውም የተ​ጻፉ ሰዎች ተነ​ሥ​ተው ምር​ኮ​ኞ​ቹን ወሰዱ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ራቁ​ታ​ቸ​ውን ለነ​በ​ሩት ሁሉ ከም​ር​ኮው አለ​በ​ሱ​አ​ቸው፤ አጐ​ና​ጸ​ፉ​አ​ቸ​ውም፤ ጫማም በእ​ግ​ራ​ቸው አደ​ረ​ጉ​ላ​ቸው፤ መገ​ቡ​አ​ቸ​ውም፤ አጠ​ጡ​አ​ቸ​ውም፤ ቀቡ​አ​ቸ​ውም፤ ደካ​ሞ​ቹ​ንም ሁሉ በአ​ህ​ዮች ላይ አስ​ቀ​መ​ጡ​አ​ቸው፤ ዘን​ባ​ባም ወዳ​ለ​በት ከተማ ወደ ኢያ​ሪኮ ወደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው አመ​ጡ​አ​ቸው፤ ወደ ሰማ​ር​ያም ተመ​ለሱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች