የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ሳሙኤል 22:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሳ​ኦል እጅና ከጠ​ላ​ቶቹ ሁሉ እጅ ባዳ​ነው ቀን የዚ​ህን መዝ​ሙር ቃል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገረ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ከጠላቶቹ ሁሉና ከሳኦል እጅ በታደገው ጊዜ፣ ዳዊት የዚህን መዝሙር ቃል ለእግዚአብሔር ዘመረ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ ከጠላቶቹ ሁሉና ከሳኦልም እጅ በታደገው ጊዜ፥ ዳዊት የዚህን መዝሙር ቃል ለጌታ ዘመረ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ዳዊትን ከሳኦልና ከሌሎቹም ጠላቶቹ እጅ በመታደግ ባዳነው ጊዜ ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር ክብር ዘመረ፦

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዳዊትም እግዚአብሔር ከሳኦል እጅና ከጠላቶቹ እጅ ሁሉ ባዳነው ቀን የዚህን ቅኔ ቃል ለእግዚአብሔር ተናገረ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ሳሙኤል 22:1
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ናታ​ንም ዳዊ​ትን አለው፥ “ይህን ያደ​ረገ ያ ሰው አንተ ነህ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ንጉሥ ልት​ሆን ቀባ​ሁህ፤ ከሳ​ኦ​ልም እጅ አዳ​ን​ሁህ፤


ከጠ​ላ​ቶቼ የሚ​ያ​ወ​ጣኝ እርሱ ነው፤ በእ​ኔም ላይ ከቆሙ ከፍ ከፍ ታደ​ር​ገ​ኛ​ለህ፤ ከግ​ፈ​ኛም ሰው ታድ​ነ​ኛ​ለህ።


በዚ​ያም ቀን ዳዊት በአ​ሳ​ፍና በወ​ን​ድ​ሞቹ እጅ እግ​ዝ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዲ​ያ​መ​ሰ​ግኑ አስ​ቀ​ድሞ ትእ​ዛ​ዝን ሰጠ።


በግፍ የሚ​ጠ​ሉኝ በላዬ ደስ አይ​በ​ላ​ቸው፥ በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ሉ​ኝና በዐ​ይ​ና​ቸው የሚ​ጠ​ቃ​ቀ​ሱ​ብ​ኝም።


የመ​ድ​ኀ​ኒቴ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ከደም አድ​ነኝ፥ አን​ደ​በ​ቴም በአ​ንተ ጽድቅ ደስ ይለ​ዋል።


በዚያ ጊዜም ሙሴና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ይህን መዝ​ሙር ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘመሩ፤ እን​ዲ​ህም ብለው ተና​ገሩ፦ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዘ​ም​ራ​ለን፤ በክ​ብር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና፤ ፈረ​ሱ​ንና ፈረ​ሰ​ኛ​ውን በባ​ሕር ጣለ።


እር​ሱም እን​ዲህ ካለ ሞት አዳ​ነን፤ ያድ​ነ​ን​ማል፤ አሁ​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ድ​ነን እር​ሱን እን​ታ​መ​ና​ለን።


ሙሴም በእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ ጆሮ የዚ​ህ​ችን መዝ​ሙር ቃሎች እስከ መጨ​ረ​ሻው ድረስ ተና​ገረ።


ጌታም ከክፉ ነገር ሁሉ ያድነኛል፤ ለሰማያዊውም መንግሥት ይጠብቀኛል፤ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።


በዚ​ያ​ችም ቀን ዲቦ​ራና የአ​ቢኒ​ሔም ልጅ ባርቅ እን​ዲህ ብለው ዘመሩ፦


ዳዊ​ትም በም​ድረ በዳ በጠ​ባቡ በማ​ሴ​ሬም ይኖር ነበር፥ በአ​ው​ክ​ሞ​ዲስ ውስ​ጥም በዚፍ ተራራ ምድረ በዳ ተቀ​መጠ፤ ሳኦ​ልም ሁል​ጊዜ ይፈ​ል​ገው ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በእጁ አሳ​ልፎ አል​ሰ​ጠ​ውም።


አሁ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ማንን ለማ​ሳ​ደድ ወጥ​ተ​ሀል? አን​ተስ ማንን ታሳ​ድ​ዳ​ለህ? የሞተ ውሻን ታሳ​ድ​ዳ​ለ​ህን? ወይስ ቍን​ጫን ታሳ​ድ​ዳ​ለህ?


የሚ​ያ​ሳ​ድ​ድ​ህና ነፍ​ስ​ህን የሚሻ ሰው ቢነሣ፥ የጌ​ታዬ ነፍስ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በሕ​ይ​ወት ማሰ​ሪያ የታ​ሰ​ረች ትሆ​ና​ለች፤ የጠ​ላ​ቶ​ችህ ነፍስ ግን በወ​ን​ጭፍ እን​ደ​ሚ​ወ​ነ​ጨፍ ትሁን።


ነፍ​ስ​ህም ዛሬ በዐ​ይኔ ፊት እንደ ከበ​ረች እን​ዲሁ ነፍሴ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትክ​በር፤ ከመ​ከ​ራም ሁሉ ይሰ​ው​ረኝ፤ ያድ​ነ​ኝም።”


ዳዊ​ትም በልቡ፥ “አንድ ቀን በሳ​ኦል እጅ እሞ​ታ​ለሁ፤ ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ምድር ከመ​ሸሸ በቀር የሚ​ሻ​ለኝ የለም፤ ሳኦ​ልም በእ​ስ​ራ​ኤል አው​ራጃ ሁሉ እኔን መሻት ይተ​ዋል፤ እን​ዲ​ሁም ከእጁ እድ​ና​ለሁ” አለ።