Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 22:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር ከጠላቶቹ ሁሉና ከሳኦል እጅ በታደገው ጊዜ፣ ዳዊት የዚህን መዝሙር ቃል ለእግዚአብሔር ዘመረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጌታ ከጠላቶቹ ሁሉና ከሳኦልም እጅ በታደገው ጊዜ፥ ዳዊት የዚህን መዝሙር ቃል ለጌታ ዘመረ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር ዳዊትን ከሳኦልና ከሌሎቹም ጠላቶቹ እጅ በመታደግ ባዳነው ጊዜ ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር ክብር ዘመረ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ዳዊ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሳ​ኦል እጅና ከጠ​ላ​ቶቹ ሁሉ እጅ ባዳ​ነው ቀን የዚ​ህን መዝ​ሙር ቃል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ገረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ዳዊትም እግዚአብሔር ከሳኦል እጅና ከጠላቶቹ እጅ ሁሉ ባዳነው ቀን የዚህን ቅኔ ቃል ለእግዚአብሔር ተናገረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 22:1
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚያም ናታን፣ ዳዊትን እንዲህ አለው፤ “ያ ሰው አንተ ነህ፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤ ‘በእስራኤል ላይ ንጉሥ ትሆን ዘንድ ቀባሁህ፤ ከሳኦልም እጅ ታደግሁህ፤


እርሱ ከጠላቶቼ እጅ ነጻ ያወጣኛል። አንተ ከጠላቶቼ በላይ ከፍ ከፍ አደረግኸኝ፤ ከጨካኝ ሰዎችም እጅ ታደግኸኝ።


በዚያም ቀን ዳዊት በመጀመሪያ ለአሳፍና ለሥራ ጓደኞቹ ይህን የእግዚአብሔር ምስጋና መዝሙር ሰጠ፤


የጻድቅ መከራው ብዙ ነው፤ እግዚአብሔር ግን ከሁሉም ያድነዋል።


“ለእግዚአብሔር የምስጋና መሥዋዕት አቅርብ፤ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ።


ከዚያም ሙሴና እስራኤላውያን ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፤ “ከፍ ከፍ ብሎ ከብሯልና፣ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን፣ በባሕር ውስጥ ጥሏልና።


እርሱ እንዲህ ካለው የሞት አደጋ አድኖናል፤ ያድነናልም፤ ወደ ፊትም ደግሞ እንደሚያድነን ተስፋችንን በርሱ ላይ ጥለናል።


ሙሴም የዚህን መዝሙር ቃል ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ፣ ለተሰበሰበው የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በጆሯቸው እንዲህ ሲል አሰማ፦


ጌታ ከክፉ ነገር ሁሉ ያድነኛል፤ ወደ ሰማያዊው መንግሥቱም በሰላም ያደርሰኛል፤ ለርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን። አሜን።


በዚያ ዕለት ዲቦራና የአቢኒኤም ልጅ ባርቅ ይህን ቅኔ ተቀኙ፤


ዳዊት በምድረ በዳ ባሉ ምሽጎችና በዚፍ ምድረ በዳ ኰረብቶች ተቀመጠ፤ ሳኦልም በየዕለቱ ይከታተለው ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ዳዊትን አሳልፎ አልሰጠውም።


አሁንም እግዚአብሔር ዳኛ ሆኖ በመካከላችን ይፍረድ፤ ጕዳዬን ተመልክቶ እርሱው ይሟገትልኝ፤ እኔንም ከእጅህ ነጻ በማውጣት እውነተኛ መሆኔን ይግለጠው።”


ማንም ሰው ሕይወትህን ለማጥፋት ቢያሳድድህ እንኳ፣ የጌታዬ ሕይወት በሕያዋን አንድነት እስራት ውስጥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ በሰላም ትጠበቃለች፤ የጠላቶችህን ሕይወት ግን፣ እንደ ወንጭፍ ድንጋይ ይወነጭፋል።


እነሆ፤ ዛሬ ሕይወትህ በፊቴ እንደ ከበረች ሁሉ፣ የእኔም ሕይወት በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረች ትሁን፤ ከመከራም ሁሉ ያድነኝ።”


ዳዊት ግን በልቡ፣ “ከእነዚህ ቀናት በአንዱ በሳኦል እጅ መገደሌ ስለማይቀር፣ የሚበጀኝ ወደ ፍልስጥኤማውያን ምድር መሸሽ ብቻ ነው፤ ከዚያ በኋላም ሳኦል በእስራኤል ሁሉ እኔን ማሳደዱን ይተዋል፤ እኔም ከእጁ አመልጣለሁ” ብሎ ዐሰበ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች