Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 22:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እንዲህም አለ፤ “እግዚአብሔር ዐለቴ፣ መጠጊያዬና ታዳጊዬ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እንዲህም አለ፤ ጌታ ዐለቴ ዐምባዬና ታዳጊዬ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እግዚአብሔር አለቴ፥ አምባዬ የደኅንነቴ ኀይል፥ ጠንካራ ምሽጌ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እን​ዲ​ህም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዓለቴ፥ አም​ባ​ዬም፥ መድ​ኀ​ኒ​ቴም ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እንዲህም አለ፦ እግዚአብሔር ዓለቴ አምባዬ መድኃኒቴ ነው፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 22:2
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእግዚአብሔር በቀር ማን አምላክ አለ? ከአምላካችንስ በቀር ዐለት ማን ነው?


ኀይልን የሚያስታጥቀኝ፣ መንገዴንም የሚያቀና እርሱ አምላኬ ነው።


የእስራኤል አምላክ ተናገረ፤ የእስራኤልም ዐለት እንዲህ አለኝ፤ ‘ሰዎችን በጽድቅ የሚገዛ፣ በፈሪሀ እግዚአብሔርም የሚያስተዳድር፣


እርሱ አፍቃሪ አምላኬና ጽኑ ዐምባዬ ነው፤ ምሽጌና ታዳጊዬ፣ የምከለልበትም ጋሻዬ ነው፤ ሕዝቤን የሚያስገዛልኝም እርሱ ነው።


አንተ ዐለቴና መጠጊያዬ ነህና፣ ስለ ስምህ ስትል ምራኝ፤ መንገዱንም ጠቍመኝ።


እግዚአብሔር ዐለቴን፣ “ለምን ረሳኸኝ? ጠላትስ እያስጨነቀኝ፣ ለምን በሐዘን እመላለሳለሁ?” እለዋለሁ።


ምን ጊዜም የምሸሽበት፣ መጠጊያ ዐለት ሁነኝ፤ አንተ ዐለቴ ምሽጌ ነህና፣ ታድነኝ ዘንድ ትእዛዝህ ይውጣ።


እግዚአብሔርን፣ “መጠጊያዬ፣ ምሽጌ፣ የምታመንብህ አምላኬ” እለዋለሁ።


የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤ ጻድቅ ወደ እርሱ በመሮጥ ተገን ያገኝበታል።


አንተ ጴጥሮስ ነህ፤ በዚህ ዐለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፤ የገሃነም ደጆችም አያሸንፏትም።


እርሱ ዐለት፣ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ ትክክል ነው፤ የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፣ ቀጥተኛና ጻድቅ አምላክም እርሱ ነው።


“እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ማንም የለም፤ ከአንተም በቀር ሌላ የለም፤ እንደ አምላካችን ያለ ዐለት የለም።


ሳኦልና ሰዎቹም ዳዊትን ሊፈልጉት ሄዱ፤ እርሱም ይህን በሰማ ጊዜ፣ ወደ ዐለቱ ወርዶ በማዖን ምድረ በዳ ተቀመጠ። ሳኦልም ይህን እንደ ሰማ፣ ዳዊትን በማሳደድ ወደ ማዖን ምድረ በዳ ዘልቆ ገባ።


ስለዚህ ሳኦል ከመላው እስራኤል የተመረጡ ሦስት ሺሕ ሰዎችን ይዞ ዳዊትንና ሰዎቹን ለመፈለግ “የሜዳ ፍየሎች ዐለት” ወደተባለው ቦታ አቅራቢያ ሄደ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች