“ኦርዮ ወደ ቤቱ አልሄደም” ብለው ለዳዊት ነገሩት፤ ዳዊትም ኦርዮን፥ “አንተ ከመንገድ የመጣህ አይደለህምን? ስለምን ወደ ቤትህ አልወረድህም?” አለው።
2 ሳሙኤል 11:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኦርዮም ለዳዊት፥ “የእግዚአብሔር ታቦትና እስራኤል፥ ይሁዳም በድንኳን ተቀምጠዋል፤ ጌታዬ ኢዮአብና የጌታዬም አገልጋዮች በሰፊ ሜዳ ሰፍረዋል፤ እኔ ልበላና ልጠጣ ወይስ ከሚስቴ ጋር ልተኛ ወደ ቤቴ እሄዳለሁን? በሕይወትህና በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ይህን ነገር አላደርገውም” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኦርዮም ዳዊትን፣ “ታቦቱ፣ እስራኤልና ይሁዳ በድንኳን ሆነው፣ ጌታዬ ኢዮአብና የጌታዬም ሰዎች አውላላ ሜዳ ላይ ሰፍረው፣ ለመብላትና ለመጠጣት እንዲሁም ከሚስቴ ጋራ ለመተኛት እንዴት ወደ ቤቴ እሄዳለሁ? እንዲህ ያለውን ነገር እንደማላደርገው በነፍስህ እምላለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኦርዮም ዳዊትን፥ “ታቦቱ፥ እስራኤልና ይሁዳ በድንኳን ሆነው፥ ጌታዬ ኢዮአብና የጌታዬም ሰዎች አውላላ ሜዳ ላይ ሰፍረው፥ ለመብላትና ለመጠጣት እንዲሁም ከሚስቴ ጋር ለመተኛት እንዴት ወደ ቤቴ እሄዳለሁ? በሕይወትህና በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ይህን ነገር አላደርገውም” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኦርዮም እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፤ “የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች በድንኳን ሰፍረው በጦር ሜዳ ይገኛሉ፤ የቃል ኪዳኑም ታቦት ከእነርሱ ጋር ነው፤ የጦር አለቃዬ ኢዮአብና የእርሱም የጦር መኰንኖች በሜዳ ሰፍረዋል፤ ታዲያ እኔ ወደ ቤቴ ሄጄ መብላት፥ መጠጣት፥ ከሚስቴም ጋር መተኛት እንዴት ይቻለኛል? ይህን የመሰለ ነገር ከቶ እንደማላደርግ በአንተ ሕይወት እምላለሁ!” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኦርዮም ዳዊትን፦ ታቦቱና እስራኤል ይሁዳም በጎጆ ተቀምጠዋል፥ ጌታዬ ኢዮአብና የጌታዬም ባሪያዎች በሰፊ ሜዳ ሰፍረዋል እኔ ልበላና ልጠጣ ወይስ ከሚስቴ ጋር ልተኛ ወደ ቤቴ እሄዳላሁን? በሕይወትህና በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ይህን ነገር አላደርገውም አለው። |
“ኦርዮ ወደ ቤቱ አልሄደም” ብለው ለዳዊት ነገሩት፤ ዳዊትም ኦርዮን፥ “አንተ ከመንገድ የመጣህ አይደለህምን? ስለምን ወደ ቤትህ አልወረድህም?” አለው።
ንጉሡም፥ “በዚህ ሁሉ ነገር የኢዮአብ እጅ ከአንቺ ጋር አለን?” አላት። ሴቲቱም ንጉሡን አለችው፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ጌታዬ ንጉሥ ከተናገረው ነገር ሁሉ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ሊል የሚችል የለም፤ አገልጋይህ ኢዮአብ አዝዞኛል፤ ይህንም ቃል ሁሉ በአገልጋይህ አፍ አደረገው።
ዳዊትም አቢሳን፥ “አሁን አቤሴሎም ከአደረገብን ይልቅ የከፋ የሚያደርግብን የቢኮሪ ልጅ ሳቡሄ ነው፤ እርሱ የተመሸጉትን ከተሞች አግኝቶ ከዐይናችን እንዳይሰወር፥ አንተ የጌታህን ብላቴኖች ወስደህ አሳድደው” አለው።
ንጉሡ ነቢዩ ናታንን፥ “እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጬአለሁ፤ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ተቀምጣለች” አለው።
የእስራኤልን ልጆች ከግብፅ ምድር ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በድንኳንና በማደሪያ እሄድና እመላለስ ነበር እንጂ በቤት አልተቀመጥሁምና፥
እንግዲህ እኔ መምህራችሁና ጌታችሁ ስሆን እግራችሁን ካጠብኋችሁ እናንተም እንዲሁ የባልጀሮቻችሁን እግር ልታጥቡ ይገባችኋል።
እርስዋም አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ በዚህ በፊትህ ቆማ የነበረች ሴት እኔ ነኝ።
ሳኦልም ዳዊትን ፍልስጥኤማዊውን ሊዋጋ ሲወጣ ባየ ጊዜ ለሠራዊቱ አለቃ ለአቤኔር፥ “አቤኔር ሆይ፥ ይህ ብላቴና የማን ልጅ ነው?” አለው። አቤኔርም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ አላውቅም” አለ።
ዳዊትም፥ “እኔ በፊትህ ሞገስን እንዳገኘሁ አባትህ በእውነት ያውቃል፤ እርሱም፦ ዮናታን እንዳይቃወም አይወቅ ይላል፤ ነገር ግን ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ፤ እኔ እንዳልሁት በእኔና በሞት መካከል አንድ ርምጃ ያህል ቀርቶአል” ብሎ ማለ።
አሁንም ጌታዬ ሆይ! ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ወደ ንጹሕ ደም እንዳትገባና፥ እጅህን እንድታድን የከለከለህ እግዚአብሔር ነው፤ አሁንም ጠላቶችህና በጌታዬ ላይ ክፉ የሚሹ ሁሉ እንደ ናባል ይሁኑ።
ሕዝቡም ወደ ሴሎ ላኩ፤ በኪሩቤልም ላይ የሚቀመጠውን የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከዚያ አመጡ፤ ሁለቱም የዔሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ ከእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ጋር በዚያ ነበሩ።