Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 17:55 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

55 ሳኦ​ልም ዳዊ​ትን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን ሊዋጋ ሲወጣ ባየ ጊዜ ለሠ​ራ​ዊቱ አለቃ ለአ​ቤ​ኔር፥ “አቤ​ኔር ሆይ፥ ይህ ብላ​ቴና የማን ልጅ ነው?” አለው። አቤ​ኔ​ርም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ አላ​ው​ቅም” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

55 ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ለመግጠም በሚሄድበት ጊዜ ሳኦል ተመልክቶ የሰራዊቱን አዛዥ አበኔርን፣ “አበኔር ሆይ፤ ይህ ልጅ የማን ነው?” ሲል ጠየቀው። አበኔርም፣ “ንጉሥ ሆይ፤ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ አላውቅም” ብሎ መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

55 ዳዊት ፍልስጥኤማዊውን ለመግጠም ሲሄድ ሳኦል ተመልክቶ የሠራዊቱን አዛዥ አበኔርን፥ “አበኔር ሆይ፤ ይህ ልጅ የማን ነው?” ሲል ጠየቀው። አበኔርም፥ “ንጉሥ ሆይ፤ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፤ አላውቅም” ብሎ መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

55 ዳዊት ጎልያድን ለመውጋት በሚሄድበት ጊዜ ሳኦል ተመልክቶ የጦሩን አዛዥ አበኔርን “ይህ የማን ልጅ ነው?” ሲል ጠየቀው። አበኔርም “ንጉሥ ሆይ! በሕይወትህ እምላለሁ፤ የማን ልጅ እንደ ሆነ ገና አላወቅሁም” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

55 ሳኦልም ዳዊትን ወደ ፍልስጥኤማዊው ሲወጣ ባየው ጊዜ ለሠራዊቱ አለቃ ለአበኔር፦ አበኔር ሆይ፥ ይህ ብላቴና የማን ልጅ ነው? አለው። አበኔርም፦ ንጉሥ ሆይ፥ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፥ አላውቅም አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 17:55
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ታናሽ ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ከአ​ላ​መ​ጣ​ችሁ በቀር ‘የፈ​ር​ዖ​ንን ሕይ​ወት!’ ከዚህ አት​ወ​ጡም።


እር​ስ​ዋም አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ጸ​ለይ በዚህ በፊ​ትህ ቆማ የነ​በ​ረች ሴት እኔ ነኝ።


የሳ​ኦ​ልም ሚስት ስም የአ​ኪ​ማ​ኦስ ልጅ አኪ​ና​ሆም ነበ​ረች፤ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ስም የሳ​ኦል አጎት የኔር ልጅ አቤ​ኔር ነበረ።


ልኮም አስ​መ​ጣው፤ እር​ሱም ቀይ፥ ዐይ​ኑም የተ​ዋበ፥ መል​ኩም ያማረ ነበረ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ይህ መል​ካም ነውና ተነ​ሥ​ተህ ዳዊ​ትን ቅባው” አለው።


ዳዊ​ትም የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ውን ራስ ይዞ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አመ​ጣው፤ ጋሻና ጦሩን ግን በድ​ን​ኳኑ ውስጥ አኖ​ረው።


ንጉ​ሡም፥ “ይህ ብላ​ቴና የማን ልጅ እንደ ሆነ አንተ ጠይ​ቅና ዕወቅ” አለው።


ሳኦ​ልም፥ “አንተ ብላ​ቴና የማን ልጅ ነህ?” አለው ዳዊ​ትም፥ “እኔ የቤተ ልሔሙ የባ​ሪ​ያህ የእ​ሴይ ልጅ ነኝ” ብሎ መለሰ።


ዳዊ​ትም በቀ​ስታ ተነ​ሥቶ ሳኦል ወደ ሰፈ​ረ​በት ቦታ መጣ፤ ሳኦ​ልና የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ የኔር ልጅ አቤ​ኔ​ርም የተ​ኙ​በ​ትን ስፍራ አየ፤ ሳኦ​ልም በድ​ን​ኳን ውስጥ ተኝቶ ነበር፤ ሕዝ​ቡም በዙ​ሪ​ያው ሰፍሮ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች