Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 11:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 “ኦርዮ ወደ ቤቱ አል​ሄ​ደም” ብለው ለዳ​ዊት ነገ​ሩት፤ ዳዊ​ትም ኦር​ዮን፥ “አንተ ከመ​ን​ገድ የመ​ጣህ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? ስለ​ምን ወደ ቤትህ አል​ወ​ረ​ድ​ህም?” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ዳዊት፣ “ኦርዮን ወደ ቤቱ አልሄደም” መባሉን ሲሰማ ኦርዮን፣ “ከመንገድ ገና አሁን መግባትህ አይደለምን? ወደ ቤትህ ያልሄድኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ዳዊት፥ “ኦርዮ ወደ ቤቱ አልሄደም” መባሉን ሲሰማ ኦርዮንን፥ “ከመንገድ ገና አሁን መግባትህ አይደለምን? ወደ ቤትህ ያልሄድኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ኦርዮ ወደ ቤቱ አለመሄዱን ዳዊት በሰማ ጊዜ “ብዙ ጊዜ ከቤተሰብህ ተለይተህ እነሆ አሁን ገና መመለስህ ነው፤ ታዲያ ወደ ቤትህ ያልሄድከው ስለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ኦርዮ ወደ ቤቱ አልሄደም ብለው ለዳዊት ነገሩት፥ ዳዊትም ኦርዮን፦ አንተ ከመንገድ የመጣህ አይደለምን? ስለ ምን ወደ ቤትህ አልወረድህም? አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 11:10
3 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኦር​ዮም ለዳ​ዊት፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦ​ትና እስ​ራ​ኤል፥ ይሁ​ዳም በድ​ን​ኳን ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ጌታዬ ኢዮ​አ​ብና የጌ​ታ​ዬም አገ​ል​ጋ​ዮች በሰፊ ሜዳ ሰፍ​ረ​ዋል፤ እኔ ልበ​ላና ልጠጣ ወይስ ከሚ​ስቴ ጋር ልተኛ ወደ ቤቴ እሄ​ዳ​ለ​ሁን? በሕ​ይ​ወ​ት​ህና በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ! ይህን ነገር አላ​ደ​ር​ገ​ውም” አለው።


ኦርዮ ግን ከጌ​ታው አገ​ል​ጋ​ዮች ሁሉ ጋር በን​ጉሥ ቤት ደጅ ተኛ፤ ወደ ቤቱም አል​ወ​ረ​ደም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ነቢዩ ናታ​ንን ወደ ዳዊት ላከ፤ ወደ እር​ሱም መጥቶ አለው፥ “በአ​ንድ ከተማ አንዱ ባለ​ጠጋ፥ አን​ዱም ድሃ የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች