ነፍስና ትንፋሽ ለሌላቸው፥ ክፉ ነገር ያደረገባቸውን ለማይበቀሉ፥ በጎ ነገር ላደረገላቸውም በጎ ነገርን ለማያደርጉ ለጣዖቶችህ እንደ ፈጣሪያችሁ እንደ እግዚአብሔር የምትሠዉላቸውና የምትሰግዱላቸው አንተና ካህናትህ እስከ ዘለዓለም ድረስ ከእርሷ መውጫ የላችሁም።