ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ መቃብያን ካልእ 7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 የፈጠራችሁ እግዚአብሔርን የማታውቁ፥ ትእዛዙንና ቃሉንም የማትጠብቁ አንተና እንደ አንተ ያሉት ወዮላችሁ! በሲኦል ጭንቅም ተይዛችሁ በተገረፋችሁ ጊዜ በማይረባ ጸጸት ትጸጸቱ ዘንድ አላችሁና። 2 ነፍስና ትንፋሽ ለሌላቸው፥ ክፉ ነገር ያደረገባቸውን ለማይበቀሉ፥ በጎ ነገር ላደረገላቸውም በጎ ነገርን ለማያደርጉ ለጣዖቶችህ እንደ ፈጣሪያችሁ እንደ እግዚአብሔር የምትሠዉላቸውና የምትሰግዱላቸው አንተና ካህናትህ እስከ ዘለዓለም ድረስ ከእርሷ መውጫ የላችሁም። 3 እናንተንና የአማልክቶቻችሁን አገልጋዮች፥ እናንተንም የሚያዝዙ አጋንንትን ወደ ገሃነመ እሳት ያወርዳችሁ ዘንድ እንደ እናንተ ያሉ የሰነፎችን ልቡና ለማሳት ሰይጣን በውስጣቸው የሚናገርባቸው የሰው እጅ ሥራ ናቸውና። 4 የሚረባችሁ እንደሌለ አታውቁምና ትበድላላችሁ፤ ትስታላችሁም። 5 ከእናንተስ ለምግባችሁ እግዚአብሔር የፈጠራቸው እንስሳት፥ አውሬዎችና ውሾችም ይሻላሉ። እነርሱ ከአንዲት ሞት በቀር ዳግመኛ ኵነኔ የለባቸውምና። 6 እናንተ ግን ትሞታላችሁ፤ ዳግመኛም እስከ ዘለዓለም ድረስ መውጫ በሌለባት በገሃነም እንቅጥቅጥ ይፈርድባችኋል። 7 ይኸንም ተናግረው ሄዱ፤ ከእርሱም ተሰወሩ። 8 ያ ጺሩጻይዳን ግን በጽኑ ፍርሀት ተይዞ ሲንቀጠቀጥ አደረ፤ እስኪነጋም ድረስ አልተወውም። 9 ከዚህም በኋላ የጻድቃንን ሬሳዎች ወደ ጣለበት ቦታ ሄደ፤ ነገር ግን አላገኛቸውም፤ ይቀብራቸው ዘንድ ወድዶአልና። ነገር ግን ሄዶ ሬሳቸውን እንዳይነካ እግዚአብሔር ሰውሯቸዋልና አጣቸው። |