አንገትህን አደንድነሃልና ራስህንም በከተማዬ ላይ ከፍ ከፍ አድርገሃልና፥ ይህን ነገር እንደ ዐይን ጥቅሻ ፈጥኜ ባደረግሁ ጊዜ እኔ ፈጣሪህ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቀኛለህ፤ አንተ በፊቴ እሳት እንደሚበላው በነፋስ ፊት እንዳለ ሣር ነህና፥ ዓውሎ ነፋስም ከምድር አፍሶ እንደሚበትነው ትቢያ ነህና አንተ በእኔ ዘንድ እንዲሁ ነህ።