የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ነገሥት 3:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነገር ግን እስ​ራ​ኤ​ልን ያሳ​ታ​ቸ​ውን የና​ባ​ጥን ልጅ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምን ኀጢ​አት ተከ​ተለ፤ እር​ሱ​ንም አል​ተ​ወም።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም እስራኤልን ባሳተበት ኀጢአት ተያዘ፤ ከዚያም አልተላቀቀም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይህም ሆኖ ከእርሱ በፊት እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራው የናባጥ ልጅ የንጉሥ ኢዮርብዓምን አምልኮ ተከተለ እንጂ አላስወገደውም።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይህም ሆኖ ከእርሱ በፊት እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራው የናባጥ ልጅ የንጉሥ ኢዮርብዓምን አምልኮ ተከተለ እንጂ አላስወገደውም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን እስራኤልን ባሳታቸው በናባጥ ልጅ በኢዮርብዓም ኀጢአት ተያዘ፤ ከእርሱም አልራቀም።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ነገሥት 3:3
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚ​ህም በኋላ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ከክ​ፋቱ አል​ተ​መ​ለ​ሰም፤ ነገር ግን ለኮ​ረ​ብ​ታ​ዎቹ መስ​ገ​ጃ​ዎች አብ​ልጦ ከሕ​ዝብ ሁሉ የጣ​ዖት ካህ​ና​ትን ሾመ፤ የሚ​ወ​ድ​ደ​ው​ንም ሁሉ ይቀ​ድስ ነበር፤ እር​ሱም ለኮ​ረ​ብ​ቶቹ መስ​ገ​ጃ​ዎች ካህን ይሆን ነበር።


ስለ በደ​ለ​ውና እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ስላ​ሳ​ተ​በት ስለ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት እስ​ራ​ኤ​ልን ይጥ​ላል።”


ከአ​ን​ተም አስ​ቀ​ድ​መው ከነ​በ​ሩት ሁሉ ይልቅ ክፉ ሠራህ፤ ታስ​ቈ​ጣ​ኝም ዘንድ ሄደህ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክ​ትና ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ትን ምስ​ሎች አደ​ረ​ግህ፤ ወደ ኋላ​ህም ተው​ኸኝ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ፤ በአ​ባ​ቱም መን​ገድ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ባሳ​ተ​በት ኀጢ​አት ሄደ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ አደ​ረገ፥ በና​ባ​ጥም ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም መን​ገድ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ባሳ​ተ​በት ኀጢ​አት ሄደ።


በና​ባ​ጥም ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት መሄድ አል​በ​ቃ​ውም፤ የሲ​ዶ​ና​ው​ያ​ን​ንም ንጉሥ የኤ​ያ​ት​ባ​ሔ​ልን ልጅ ኤል​ዛ​ቤ​ልን አገባ፤ ሄዶም በዓ​ልን አመ​ለከ ሰገ​ደ​ለ​ትም።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልን ካሳ​ተው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት አል​ራ​ቀም፤ ነገር ግን በእ​ር​ስዋ ሄደ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ያሳ​ተ​ውን የና​ባ​ጥን ልጅ የኢ​ዮ​ር​ብ​ዓ​ምን ኀጢ​አት ተከ​ተለ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም አል​ራ​ቀም።


ነገር ግን በእ​ር​ስዋ ሄዱ እንጂ እስ​ራ​ኤ​ልን ካሳ​ተ​በት ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ቤት ኀጢ​አት አል​ራ​ቁም፤ ደግ​ሞም የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ በሰ​ማ​ርያ ቆሞ ነበረ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ካሳ​ታ​ቸው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት ሁሉ አል​ራ​ቀም።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ልን ካሳ​ተው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አ​ትም አል​ራ​ቀም።


አባ​ቶ​ቹም እን​ዳ​ደ​ረ​ጉት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገር አደ​ረገ፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ካሳ​ታ​ቸው ከና​ባጥ ልጅ ከኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት አል​ራ​ቀም።


እስ​ራ​ኤ​ልም ከዳ​ዊት ቤት ተለዩ፤ የና​ባ​ጥ​ንም ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምን አነ​ገሡ፤ ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ምም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ከመ​ከ​ተል እስ​ራ​ኤ​ልን መለሰ፤ ታላ​ቅም ኀጢ​አት አሠ​ራ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ኢዮ​ር​ብ​ዓም ባደ​ረ​ገው ኀጢ​አት ሁሉ ሄዱ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በባ​ሪ​ያ​ዎቹ በነ​ቢ​ያት ሁሉ አፍ እንደ ተና​ገ​ረው እስ​ራ​ኤ​ልን ከፊቱ እስ​ኪ​ያ​ወጣ ድረስ ከእ​ር​ስዋ አል​ራ​ቁም። እስ​ራ​ኤ​ልም እስከ ዛሬ ድረስ ከም​ድሩ ወደ አሦር ፈለሰ።


ደግ​ሞም ምናሴ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዐይ​ኖች ፊት ክፉ ይሠራ ዘንድ ይሁ​ዳን ካሳ​ተ​በት ኀጢ​አት ሌላ ከዳር እስከ ዳር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እስ​ኪ​ሞ​ላት ድረስ እጅግ ብዙ ንጹሕ ደምን አፈ​ሰሰ።


ደግ​ሞም በቤ​ቴል ኮረ​ብታ የነ​በ​ረ​ውን መሠ​ዊያ፥ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ያሳተ የና​ባጥ ልጅ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ያሠ​ራ​ውን የኮ​ረ​ብ​ታ​ውን መስ​ገጃ፥ ይህ​ንም መሠ​ዊ​ያና መስ​ገጃ አፈ​ረሰ፤ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ሰባ​በረ፤ አድ​ቅ​ቆም ትቢያ አደ​ረ​ገው፤ የማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀ​ዱ​ንም አቃ​ጠ​ለው።