የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




2 ቆሮንቶስ 2:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ግ​ዲህ እያ​ዘ​ንሁ ወደ እና​ንተ እን​ዳ​ል​መጣ በልቤ ይህን ወሰ​ንሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንግዲህ ላሳዝናችሁ ስላልፈለግሁ ወደ እናንተ ዳግመኛ ላለመምጣት ወሰንሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ ዳግመኛ በጉብኝቴ እንዳላስቸግራችሁ ወደ እናንተ ላለመምጣት ቆረጥሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንግዲህ እናንተን እንዳላሳዝናችሁ በማሰብ ለጒብኝት ወደ እናንተ ተመልሼ ላለመምጣት ቊርጥ ውሳኔ አደረግሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን ዳግመኛ በኀዘን ወደ እናንተ እንዳልመጣ ስለ እኔ ቆረጥሁ።

ምዕራፉን ተመልከት



2 ቆሮንቶስ 2:1
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚ​ህም በኋላ ደቀ መዛ​ሙ​ርት እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው የሚ​ች​ሉ​ትን ያህል አወ​ጣ​ጥ​ተው በይ​ሁዳ ሀገር ለሚ​ኖ​ሩት ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው ርዳ​ታን ይልኩ ዘንድ ወሰኑ።


ሕዝ​ቡም እጅግ ታወኩ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስ​ንም ተከ​ራ​ከ​ሩ​አ​ቸው፤ ስለ​ዚህ ነገ​ርም ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስን፥ ጓደ​ኞ​ቻ​ቸ​ው​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አሉት ወደ ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስት ሊል​ኳ​ቸው ተማ​ከሩ።


በር​ና​ባ​ስም ማር​ቆስ የተ​ባ​ለ​ውን ዮሐ​ን​ስን ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይዞት ሊሄድ ወደደ።


ከተ​ሰ​ቀ​ለው ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በቀር በእ​ና​ንተ ዘንድ ሌላ ነገር እሰ​ማ​ለሁ ብዬ አል​ጠ​ረ​ጠ​ር​ሁም ነበር።


እን​ዴት ሆኜ ወደ እና​ንተ ልመጣ ትወ​ዳ​ላ​ችሁ? በበ​ትር ነውን? ወይስ በፍ​ቅ​ርና በቅ​ን​ነት መን​ፈስ?


እኔ በሥ​ጋዬ ከእ​ና​ንተ ጋር ባል​ኖር፥ በመ​ን​ፈሴ ከእ​ና​ንተ ጋር አለሁ፤ እነሆ፥ ከእ​ና​ንተ ጋር እንደ አለሁ ሆኜ፥ ይህን ሥራ የሠ​ራ​ውን እፈ​ር​ድ​በ​ታ​ለሁ።


እኔ ለእ​ና​ንተ በመ​ራ​ራት ወደ ቆሮ​ን​ቶስ እን​ዳ​ል​መ​ጣሁ፥ ስለ ራሴ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምስ​ክር አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።


ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለማ​ፍ​ረስ ያይ​ደለ ለማ​ነጽ በሰ​ጠን ሥል​ጣን ወደ እና​ንተ በመ​ጣሁ ጊዜ ቍርጥ ነገር እን​ዳ​ላ​ደ​ር​ግ​ባ​ችሁ፥ ሥል​ጣን እን​ዳ​ለው ሰው ከእ​ና​ንተ ጋር ሳል​ኖር ይህን እጽ​ፋ​ለሁ።


ከብዙ መከ​ራና ከልብ ጭን​ቀት የተ​ነሣ በብዙ እንባ ይህን ጽፌ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ነገር ግን እጅግ እን​ደ​ም​ወ​ዳ​ችሁ እን​ድ​ታ​ውቁ ነው እንጂ እን​ድ​ታ​ዝኑ አይ​ደ​ለም።


አርጢሞንን ወይም ቲኪቆስን ወደ አንተ ስልክ፥ ወደ ኒቆጵልዮን ወደ እኔ እንድትመጣ ትጋ፤ በዚያ ልከርም ቈርጫለሁና።