1 ሳሙኤል 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍልስጥኤማውያንም እስራኤልን ለመውጋት ተሰለፉ፤ እስራኤልም ሸሹ፤ በፍልስጥኤማውያንም ፊት ድል ሆኑ፤ ጦርነት በተደረገበትም ስፍራ ከእስራኤል አራት ሺህ ሰዎች ተገደሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመግጠም ሰራዊታቸውን አሰለፉ፤ ጦርነቱ እንደ ተፋፋመም፣ እስራኤላውያን በፍልስጥኤማውያን ተሸነፉ፤ በጦርነቱም ላይ አራት ሺሕ ያህል እስራኤላውያን ተገደሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመግጠም ሠራዊታቸውን አሰለፉ፤ ጦርነቱ እንደ ተፋፋመም፥ እስራኤላውያን በፍልስጥኤማውያን ተሸነፉ፤ በጦርነቱም ላይ አራት ሺህ ያህል እስራኤላውያን ተገደሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍልስጥኤማውያንም አደጋ መጣል ጀመሩ፤ ከከባድ ጦርነት በኋላ እስራኤላውያንን ድል በመንሣት በጦር ሜዳ አራት ሺህ ሰው ገደሉባቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍልስጥኤማውያንም በእስራኤል ላይ ተሰለፉ፥ ሰልፋም በተመደበ ጊዜ እስራኤል በፍልስጥኤማውያን ፊት ተመቱ፥ ጦርነት በተደረገበትም ስፍራ ከእስራኤል አራት ሺህ የሚያህሉ ሰዎችን ገደሉ። |
ማንም ሳያሳድዳቸው ከሰይፍ እንዲሸሹ እርስ በርሳቸው ይሰነካከላሉ፤ እናንተም በጠላቶቻችሁ ፊት መቆም አትችሉም።
በዚያም ተራራ ላይ የተቀመጡ ዐማሌቃዊና ከነዓናዊ ወረዱ፤ መትተዋቸውም እስከ ኤርማ ድረስ አሳደዱአቸው። ወደ ከተማም ተመለሱ።
ስለዚህም የእስራኤል ልጆች በጠላቶቻቸው ፊት መቆም አይችሉም፤ የተረገሙ ስለሆኑ በጠላቶቻቸው ፊት ይሸሻሉ፤ እርም የሆነውንም ነገር ከመካከላችሁ ካላጠፋችሁ ከዚህ በኋላ ከእናንተ ጋር አልሆንም።
እርሱም ቆሞ ወደ እስራኤል ጭፍሮች ጮኸ፥ “ከእኛ ጋር ትዋጉ ዘንድ ለምን ወጣችሁ? እኔ ፍልስጥኤማዊ አይደለሁምን? እናንተስ የሳኦል አገልጋዮች ዕብራውያን አይደላችሁምን? ከእናንተ አንድ ሰው ምረጡ፤ ወደ እኔም ይውረድ፤
በእነዚያም ወራት እንዲህ ሆነ። ፍልስጥኤማውያን ለጦርነት በእስራኤላውያን ላይ ተሰበሰቡ። እስራኤልም ሊዋጉአቸው ወጡ፤ በአቤኔዜር አጠገብም ሰፈሩ፤ ፍልስጥኤማውያንም በአፌቅ ሰፈሩ።
ከዚህም በኋላ ተዋጉአቸው፤ እስራኤልም በፍልስጥኤማውያን ፊት ወደቁ፤ ሁሉም እያንዳንዳቸው ወደ ድንኳናቸው ሸሹ፤ እጅግም ታላቅ ግድያ ሆነ፤ ከእስራኤልም ሠላሳ ሺህ እግረኞች ወደቁ።
ሕዝቡም ወደ ሰፈር በተመለሱ ጊዜ የእስራኤል ሽማግሌዎች፥ “ዛሬ እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ፊት ስለምን ጣለን? በፊታችን እንድትሄድ፥ ከጠላቶቻችንም እጅ እንድታድነን፥ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳኑን ታቦት ከሴሎ እናምጣ” አሉ።