Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 17:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እር​ሱም ቆሞ ወደ እስ​ራ​ኤል ጭፍ​ሮች ጮኸ፥ “ከእኛ ጋር ትዋጉ ዘንድ ለምን ወጣ​ችሁ? እኔ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ አይ​ደ​ለ​ሁ​ምን? እና​ን​ተስ የሳ​ኦል አገ​ል​ጋ​ዮች ዕብ​ራ​ው​ያን አይ​ደ​ላ​ች​ሁ​ምን? ከእ​ና​ንተ አንድ ሰው ምረጡ፤ ወደ እኔም ይው​ረድ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ጎልያድ ቆሞ ለተሰለፈው የእስራኤል ሰራዊት እንዲህ ሲል ጮኾ ተናገረ፤ “ለውጊያ ተሰልፋችሁ መውጣታችሁ ስለ ምንድን ነው? እኔ ፍልስጥኤማዊ፣ እናንተም የሳኦል አገልጋዮች አይደላችሁምን? አንድ ሰው ምረጡና እኔ ወደ አለሁበት ይውረድ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጎልያድ ቆሞ ለተሰለፈው የእስራኤል ሠራዊት እንዲህ ሲል ጮኾ ተናገረ፤ “ለውጊያ ተሰልፋችሁ መውጣታችሁ ስለ ምንድነው? እኔ ፍልስጥኤማዊ፥ እናንተም የሳኦል አገልጋዮች አይደላችሁምን? አንድ ሰው ምረጡና እኔ ወደ አለሁበት ይውረድ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ጎልያድ ተነሥቶ በመቆም በእስራኤል ሠራዊት ላይ እንዲህ እያለ ይደነፋባቸው ጀመር፦ “አሁን በዚያ ቦታ ለጦርነት የተሰለፋችሁት ከቶ ምን ልታደርጉ ነው? እኔ ፍልስጥኤማዊ ነኝ፤ እናንተ ደግሞ የሳኦል ባሪያዎች ናችሁ፤ እንግዲህ ከእኔ ጋር የሚዋጋ አንድ ሰው ከወታደሮቻችሁ መካከል ምረጡና ወደ እኔ መጥቶ ይግጠመኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እርሱም ቆሞ ወደ እስራኤል ጭፍሮች ጮኸ፦ ለሰልፍ ትሠሩ ዘንድ ለምን ወጣችሁ? እኔ ፍልስጥኤማዊ፥ እናንተም የሳኦል ባሪያዎች አይደላችሁምን? ለእናንተ አንድ ሰው ምረጡ፥ ወደ እኔም ይውረድ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 17:8
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኦር​ዮም ለዳ​ዊት፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦ​ትና እስ​ራ​ኤል፥ ይሁ​ዳም በድ​ን​ኳን ተቀ​ም​ጠ​ዋል፤ ጌታዬ ኢዮ​አ​ብና የጌ​ታ​ዬም አገ​ል​ጋ​ዮች በሰፊ ሜዳ ሰፍ​ረ​ዋል፤ እኔ ልበ​ላና ልጠጣ ወይስ ከሚ​ስቴ ጋር ልተኛ ወደ ቤቴ እሄ​ዳ​ለ​ሁን? በሕ​ይ​ወ​ት​ህና በሕ​ያው ነፍ​ስህ እም​ላ​ለሁ! ይህን ነገር አላ​ደ​ር​ገ​ውም” አለው።


ኢዮ​አ​ብም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ዝቡ ላይ አሁን ባለ​በት መቶ እጥፍ ይጨ​ምር፤ የጌ​ታዬ የን​ጉሥ ዐይ​ኖ​ችም ይዩ፤ ሁሉም የጌ​ታዬ አገ​ል​ጋ​ዮች ናቸው፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ በደል ይሆን ዘንድ ይህን ነገር ጌታዬ ለምን ይሻል?” አለ።


እር​ሱም ሲነ​ጋ​ገ​ራ​ቸው፥ እነሆ፥ ጎል​ያድ የተ​ባለ ያ አር​በኛ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ የጌት ሰው ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጭፍራ መካ​ከል ወጣ፤ ቀድሞ የተ​ና​ገ​ረ​ው​ንም ቃል ተና​ገረ፤ ዳዊ​ትም ሰማ።


ዳዊ​ትም በአ​ጠ​ገቡ ለቆ​ሙት ሰዎች፦ ይህን ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ለሚ​ገ​ድል፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተግ​ዳ​ሮ​ትን ለሚ​ያ​ርቅ ሰው በውኑ ይህ ይደ​ረ​ግ​ለ​ታል? የሕ​ያው አም​ላ​ክን ጭፍ​ሮች የሚ​ገ​ዳ​ደር ይህ ያል​ተ​ገ​ረዘ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማዊ ማን ነው?” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።


ከላ​ሞ​ቻ​ችሁ፥ ከበ​ጎ​ቻ​ች​ሁና ከፍ​የ​ሎ​ች​ቻ​ች​ሁም ዐሥ​ራት ይወ​ስ​ዳል፤ እና​ን​ተም ባሪ​ያ​ዎች ትሆ​ኑ​ታ​ላ​ችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች