የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 20:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አባ​ት​ህም ቢፈ​ል​ገኝ፦ ለዘ​መ​ዶቹ ሁሉ በዚያ በቤተ ልሔም የዓ​መት መሥ​ዋ​ዕት አላ​ቸ​ውና ዳዊት ወደ ከተ​ማው ፈጥኖ ይሄድ ዘንድ አጽ​ንቶ ለም​ኖ​ኛል በለው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አባትህ ከፈለገኝ፣ ‘ለቤተ ዘመዶቹ ሁሉ ዓመታዊ መሥዋዕት የሚቀርብ ስለ ሆነ፣ ዳዊት ወደ መኖሪያ ከተማው ወደ ቤተ ልሔም ቶሎ ለመሄድ አጥብቆ ፈቃድ ጠየቀኝ’ ብለህ ንገረው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አባትህ ከፈለገኝ፥ ‘ለቤተ ዘመዶቹ ሁሉ ዓመታዊ መሥዋዕት የሚቀርብ ስለሆነ፥ ዳዊት ወደ መኖሪያ ከተማው ወደ ቤተልሔም ቶሎ ለመሄድ አጥብቆ ፈቃድ ጠየቀኝ’ ብለህ ንገረው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ምናልባት አባትህ ቢፈልገኝ በቤተሰቡ ዓመታዊ በዓል የሚከበር ስለ ሆነ ወደ ቤተልሔም እንዲሄድ እፈቅድለት ዘንድ ዳዊት እኔን አጥብቆ ለምኖኛል ብለህ ንገረው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አባትህም ቢፈልገኝ፦ ለዘመዶቹ ሁሉ በዚያ በቤተልሔም የዓመት መሥዋዕት አላቸውና ዳዊት ወደ ከተማው ፈጥኖ ይሄድ ዘንድ አጽንቶ ለምኖኛል በለው።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 20:6
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መጽ​ሐፍ ‘ክር​ስ​ቶስ ከዳ​ዊት ዘርና ከዳ​ዊት ከተማ ከቤተ ልሔም ይመ​ጣል’ ይል የለ​ምን?”


ነገር ግን አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ችሁ ሁሉ በአ​ንዱ ስሙ ይጠራ ዘንድ የመ​ረ​ጠ​ውን ስፍራ ትሻ​ላ​ችሁ፤ ወደ​ዚ​ያም ትመ​ጣ​ላ​ችሁ።


ሳኦ​ልም፥ “አንተ ብላ​ቴና የማን ልጅ ነህ?” አለው ዳዊ​ትም፥ “እኔ የቤተ ልሔሙ የባ​ሪ​ያህ የእ​ሴይ ልጅ ነኝ” ብሎ መለሰ።


ዮና​ታ​ንም ለሳ​ኦል፥ “ዳዊት ወደ ከተ​ማው ወደ ቤተ ልሔም ይሄድ ዘንድ ነግ​ሮኝ ተሰ​ና​ብ​ቶ​ኛል።


ቈነ​ጃ​ጅ​ቱም፥ “አዎን እነሆ፥ በፊ​ታ​ችሁ ነው። ዛሬ ወደ ከተ​ማ​ዪቱ መጥ​ቶ​አ​ልና፥ ዛሬም ሕዝቡ በባማ ኮረ​ብታ ላይ መሥ​ዋ​ዕት ማቅ​ረብ አለ​ባ​ቸ​ውና።