Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 20:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ዳዊ​ትም ዮና​ታ​ንን አለው፥ “እነሆ ነገ መባቻ ነው፤ በን​ጉ​ሥም አጠ​ገብ ለምሳ አል​ቀ​መ​ጥም፤ እስከ ማታ ድረስ በውጭ በሜዳ እን​ድ​ሸ​ሸግ አሰ​ና​ብ​ተኝ ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ስለዚህ ዳዊት እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ ነገ የወር መባቻ በዓል ስለ ሆነ፣ ከንጉሡ ጋራ ምሳ መብላት ይጠበቅብኛል፤ ነገር ግን እስከ ከነገ ወዲያ ማታ ድረስ ከዱር ልደበቅ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ስለዚህ ዳዊት እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ ነገ የወር መባቻ በዓል ስለሆነ፥ ከንጉሡ ጋር ምሳ መብላት ይጠበቅብኛል፤ ነገር ግን እስከ ከነገ ወዲያ ማታ ድረስ ከዱር ልደበቅ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ነገ አዲስ ጨረቃ የምትታይበት በዓል ነው፤ እኔም ከንጉሡ ጋር መብላት ይኖርብኛል፤ እስከ ነገ ወዲያ ምሽት ድረስ እንድደበቅ ፍቀድልኝ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ዳዊትም ዮናታንን አለው፦ እነሆ፥ ነገ መባቻ ነው፥ በንጉሥም አጠገብ ለምሳ አልቀመጥም፥ እስከ ሦስተኛው ቀን ማታ ድረስ በውጭ በሜዳ እንድሸሸግ አሰናብተኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 20:5
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ደግሞ በደ​ስ​ታ​ችሁ ቀን፥ በበ​ዓ​ላ​ታ​ች​ሁም ዘመን፥ በወ​ርም መባቻ፥ በሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁና በደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችሁ ላይ መለ​ከ​ቶ​ችን ንፉ፤ እነ​ር​ሱም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ ፊት ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ይሆ​ኑ​ላ​ች​ኋል፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።”


ዮና​ታ​ንም፥ “አባቴ ሳኦል ሊገ​ድ​ልህ ፈል​ጎ​አል፤ አሁን እን​ግ​ዲህ ለነ​ገው ተጠ​ን​ቅ​ቀህ ተሸ​ሸግ፤ በስ​ው​ርም ተቀ​መጥ።


“በወ​ሩም መባቻ ለእ​ግ​ዚ​አ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ፤ ከላ​ሞች ሁለት፥ አንድ አውራ በግ፥ ነው​ርም የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሰባት የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦ​ቶች፥


ለድ​ሆ​ችና ለድሃ አደ​ጎች ፍረዱ፤ ለተ​ገ​ፋ​ውና ለም​ስ​ኪኑ ጽድ​ቅን አድ​ርጉ፤


እን​ግ​ዲህ በመ​ብ​ልም ቢሆን፥ በመ​ጠ​ጥም ቢሆን፥ በልዩ ልዩ በዓ​ላ​ትም ቢሆን፥ በመ​ባ​ቻም ቢሆን፥ በሰ​ን​በ​ትም ቢሆን የሚ​ነ​ቅ​ፋ​ችሁ እን​ዳ​ይ​ኖር ተጠ​ን​ቀቁ።


ያን​ጊ​ዜም ወን​ድ​ሞች ጳው​ሎ​ስን ሸኝ​ተው ወደ ባሕር አደ​ረ​ሱት፤ ሲላ​ስና ጢሞ​ቴ​ዎስ ግን በዚ​ያው ቀሩ።


ሊደ​በ​ድ​ቡ​ትም ድን​ጋይ አነሡ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ግን ተሰ​ወ​ራ​ቸው፤ ከቤተ መቅ​ደ​ስም ወጣ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም አልፎ ሄደ።


ዐዋቂ ሰው ክፉ ሰው በኀይል ሲቀጣ አይቶ ይገሠጻል፥ አላዋቂዎች ግን ሲያልፉ ይጐዳሉ።


አቤቱ፥ የም​ስ​ጋና ስእ​ለት የም​ሰ​ጥህ ከእኔ ዘንድ ነው፤


ሦስት ቀንም ያህል ቈይ፤ ከዚ​ህም በኋላ በፈ​ለ​ገህ ጊዜ ትመ​ጣና ነገሩ በተ​ደ​ረ​ገ​በት ቀን በተ​ሸ​ሸ​ግ​ህ​በት ስፍራ ትቀ​መ​ጣ​ለህ፤ በኤ​ር​ገብ ድን​ጋ​ይም አጠ​ገብ ቈይ።


አባ​ት​ህም ቢፈ​ል​ገኝ፦ ለዘ​መ​ዶቹ ሁሉ በዚያ በቤተ ልሔም የዓ​መት መሥ​ዋ​ዕት አላ​ቸ​ውና ዳዊት ወደ ከተ​ማው ፈጥኖ ይሄድ ዘንድ አጽ​ንቶ ለም​ኖ​ኛል በለው።


እር​ሱም፥ “መባቻ ወይም ሰን​በት ያይ​ደለ ዛሬ ለምን ትሄ​ጃ​ለሽ?” አለ። እር​ስ​ዋም፥ “ደኅና ነው” አለች።


ዮና​ታ​ንም ዳዊ​ትን፥ “ነፍ​ስህ ምን ትፈ​ል​ጋ​ለች? እኔስ ምን ላድ​ር​ግ​ልህ?” አለው።


ዮና​ታ​ንም አለው፥ “ነገ መባቻ ነው፤ መቀ​መ​ጫ​ህም ባዶ ሆኖ ይገ​ኛ​ልና ትታ​ሰ​ባ​ለህ።


ዳዊ​ትም በሜ​ዳው ተሸ​ሸገ፤ መባ​ቻም በሆነ ጊዜ ንጉሡ ግብር ለመ​ብ​ላት ተቀ​መጠ።


ከመ​ባ​ቻም በኋላ በማ​ግ​ሥቱ በሁ​ለ​ተ​ኛው ቀን የዳ​ዊት ስፍራ ባዶ​ውን ነበረ፤ ሳኦ​ልም ልጁን ዮና​ታ​ንን፥ “የእ​ሴይ ልጅ ትና​ትና ዛሬ ወደ ግብር ያል​መጣ ስለ​ምን ነው?” አለው።


“እህ​ልን እን​ሸጥ ዘንድ መባ​ቻው መቼ ያል​ፋል? የኢፍ መስ​ፈ​ሪ​ያ​ው​ንም እያ​ሳ​ነ​ስን፥ ሰቅ​ሉ​ንም እያ​በ​ዛን፥ በሐ​ሰ​ተ​ኛም ሚዛን እያ​ታ​ለ​ልን፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች