Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 9:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ቈነ​ጃ​ጅ​ቱም፥ “አዎን እነሆ፥ በፊ​ታ​ችሁ ነው። ዛሬ ወደ ከተ​ማ​ዪቱ መጥ​ቶ​አ​ልና፥ ዛሬም ሕዝቡ በባማ ኮረ​ብታ ላይ መሥ​ዋ​ዕት ማቅ​ረብ አለ​ባ​ቸ​ውና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “አዎን አለ፤ እነሆ፤ ከፊታችሁ ነው፤ ፈጠን በሉ፤ ሕዝቡ በማምለኪያው ኰረብታ ላይ መሥዋዕት ስለሚያቀርብ፣ ወደ ከተማችን ገና ዛሬ መምጣቱ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እነርሱም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው፤ “አዎን አለ፤ እነሆ፤ ከፊታችሁ ነው፤ ፈጠን በሉ፤ ሕዝቡ በማምለኪያው ኰረብታ ላይ መሥዋዕት ስለሚያቀርብ፥ ወደ ከተማችን ገና ዛሬ መምጣቱ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ልጃገረዶቹም “አዎን! እነሆ፥ ሕዝቡ ዛሬ በኮረብታው ላይ መሥዋዕትን ስለሚያቀርብ ባለራእዩ ወደ ከተማይቱ መጥቶአልና ፈጥናችሁ ድረሱበት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እነርሱም፦ አዎን፥ እነሆ፥ በፊታችሁ ነው፥ ዛሬ ወደ ከተማይቱ መጥቶአልና፥ ዛሬም ሕዝቡ በኮረብታው ላይ ባለው መስገጃ መሥዋዕት ማቅረብ አለባቸውና ፈጥናችሁ ውጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 9:12
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያዕ​ቆ​ብም በተ​ራ​ራው ላይ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋ፤ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ጠራ፤ እነ​ር​ሱም በሉ፤ ጠጡም፤ በዚ​ያም በተ​ራ​ራው አደሩ።


ካህ​ኑን ሳዶ​ቅ​ንና ካህ​ና​ቱን ወን​ድ​ሞ​ቹን በገ​ባ​ዖን በኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪያ ፊት አቆ​ማ​ቸው፥


ከዚ​ያም በኋላ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ጭፍራ ወዳ​ለ​በት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኮረ​ብታ ትመ​ጣ​ለህ፤ በዚ​ያም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊው ናሴብ አለ፤ ወደ​ዚ​ያም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ በደ​ረ​ስህ ጊዜ በገ​ናና ከበሮ፥ እም​ቢ​ል​ታና መሰ​ንቆ ይዘው ትን​ቢት እየ​ተ​ና​ገሩ ከኰ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ የሚ​ወ​ርዱ የነ​ቢ​ያ​ትን ጉባኤ ታገ​ኛ​ለህ።


ሳሙ​ኤ​ልም፥ “እን​ዴት እሄ​ዳ​ለሁ? ሳኦል ቢሰማ ይገ​ድ​ለ​ኛል” አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “አን​ዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፦ ‘ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሠዋ ዘንድ መጣሁ’ በል።


የታ​መነ ካህን ለእኔ አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ በል​ቤም፥ በነ​ፍ​ሴም እን​ዳለ እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋል፤ እኔም የታ​መነ ቤት እሠ​ራ​ለ​ታ​ለሁ፤ ዘመ​ኑን ሁሉ እኔ በቀ​ባ​ሁት ሰው ፊት ይሄ​ዳል።


አባ​ት​ህም ቢፈ​ል​ገኝ፦ ለዘ​መ​ዶቹ ሁሉ በዚያ በቤተ ልሔም የዓ​መት መሥ​ዋ​ዕት አላ​ቸ​ውና ዳዊት ወደ ከተ​ማው ፈጥኖ ይሄድ ዘንድ አጽ​ንቶ ለም​ኖ​ኛል በለው።


ቤቱም በዚያ ነበ​ረና ወደ አር​ማ​ቴም ይመ​ለስ ነበር፤ በዚ​ያም በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ይፈ​ርድ ነበር፤ በዚ​ያም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሠራ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች