የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




1 ሳሙኤል 1:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በሴ​ሎም ከበሉ በኋላ ሐና ተነ​ሣች። በሴ​ሎም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆመች። ካህ​ኑም ዔሊ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ መቃን አጠ​ገብ በወ​ን​በሩ ላይ ተቀ​ምጦ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አንድ ጊዜ በሴሎ ሳሉ ከበሉና ከጠጡ በኋላ ሐና ተነሥታ ቆመች፤ በዚያ ጊዜ ካህኑ ዔሊ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መቃን አጠገብ በወንበር ላይ ተቀምጦ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሴሎ ሳሉ ከበሉና ከጠጡ በኋላ ሐና ተነሥታ ቆመች፤ በዚያ ጊዜ ካህኑ ዔሊ በጌታ ቤተ መቅደስ መቃን አጠገብ በወንበር ላይ ተቀምጦ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንድ ቀን በሴሎ መሥዋዕት ሠውተው ከበሉና ከጠጡ በኋላ ሐና ተነሣች፤ ካህኑም ዔሊ በእግዚአብሔር መቅደስ በር አጠገብ ተቀምጦ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሴሎ ከበሉና ከጠጡ በኋላም ሐና ተነሳች። ካህኑም ዔሊ በእግዚአብሔር መቅደስ መቃን አጠገብ በመንበሩ ላይ ተቀምጦ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት



1 ሳሙኤል 1:9
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉሡ ነቢዩ ናታ​ንን፥ “እኔ ከዝ​ግባ በተ​ሠራ ቤት ተቀ​ም​ጬ​አ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ግን በድ​ን​ኳን ውስጥ ተቀ​ም​ጣ​ለች” አለው።


እንደ ሥራ​ቸ​ውና እንደ ዐሳ​ባ​ቸው ክፋት ስጣ​ቸው፤ እንደ እጃ​ቸ​ውም ሥራ ክፈ​ላ​ቸው፤ ፍዳ​ቸ​ውን በራ​ሳ​ቸው ላይ መልስ።


ወደ ጥፋት ብወ​ርድ በደሜ ምን ጥቅም አለ? አፈር ያመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ልን? ጽድ​ቅ​ህ​ንም ይና​ገ​ራ​ልን?


እኔ ግን በም​ሕ​ረ​ትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገ​ባ​ለሁ፤ አን​ተን በመ​ፍ​ራት በቤተ መቅ​ደ​ስህ እሰ​ግ​ዳ​ለሁ።


ጌታው ወደ ቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈራ​ጆች ይው​ሰ​ደው፤ ወደ ደጁም፥ ወደ መቃ​ኑም አቅ​ርቦ አፍ​ን​ጫ​ውን በወ​ስፌ ይብ​ሳው፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ባሪ​ያው ይሁ​ነው።


እር​ስ​ዋም በል​ብዋ አዝና አለ​ቀ​ሰች፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸለ​የች።


ሳሙ​ኤ​ልም እስ​ኪ​ነጋ ተኛ፥ ማል​ዶም ተነ​ሥቶ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ደጅ ከፈተ። ሳሙ​ኤ​ልም ራእ​ዩን ለዔሊ መን​ገር ፈራ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መብ​ራት ገና አል​ጠ​ፋም ነበር፤ ሳሙ​ኤ​ልም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ባለ​በት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ ተኝቶ ነበር፤


በመ​ጣም ጊዜ ዔሊ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ልቡ ተና​ውጦ ነበ​ርና በመ​ን​ገድ ዳር በወ​ን​በሩ ላይ ተቀ​ምጦ ይጠ​ባ​በቅ ነበር፤ ሰው​ዬ​ውም ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ገብቶ ባወራ ጊዜ ከተ​ማ​ዪቱ ሁሉ ተጭ​ዋ​ጭ​ዋ​ኸች።