Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 1:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በሴሎ ሳሉ ከበሉና ከጠጡ በኋላ ሐና ተነሥታ ቆመች፤ በዚያ ጊዜ ካህኑ ዔሊ በጌታ ቤተ መቅደስ መቃን አጠገብ በወንበር ላይ ተቀምጦ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 አንድ ጊዜ በሴሎ ሳሉ ከበሉና ከጠጡ በኋላ ሐና ተነሥታ ቆመች፤ በዚያ ጊዜ ካህኑ ዔሊ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መቃን አጠገብ በወንበር ላይ ተቀምጦ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 አንድ ቀን በሴሎ መሥዋዕት ሠውተው ከበሉና ከጠጡ በኋላ ሐና ተነሣች፤ ካህኑም ዔሊ በእግዚአብሔር መቅደስ በር አጠገብ ተቀምጦ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በሴ​ሎም ከበሉ በኋላ ሐና ተነ​ሣች። በሴ​ሎም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆመች። ካህ​ኑም ዔሊ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ መቃን አጠ​ገብ በወ​ን​በሩ ላይ ተቀ​ምጦ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በሴሎ ከበሉና ከጠጡ በኋላም ሐና ተነሳች። ካህኑም ዔሊ በእግዚአብሔር መቅደስ መቃን አጠገብ በመንበሩ ላይ ተቀምጦ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 1:9
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነቢዩን ናታንን፥ “እነሆ፤ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤተ መንግሥት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል” አለው።


ጌታን አንዲት ነገር ለመንሁት እርሷንም እሻለሁ፥ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በጌታ ቤት እኖር ዘንድ፥ ጌታን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።


የጌታ ድምፅ ዋላዎችን ያጠነክራቸዋል፥ ጫካዎቹንም ይገልጣል፥ ሁሉም በመቅደሱ፦ ምስጋና ይላል።


ሐሰትን የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለህ፥ ደም አፍሳሹንና ሸንጋዩን ሰው ጌታ ይጸየፋል።


ጌታው ወደ እግዚአብሔር ያቅርበው፥ ወደ በሩ ወይም ወደ መቃኑ አቅርቦ ጆሮውን በወስፌ ይብሳው፤ ለዘለዓለምም ያገልግለው።


እርሷም ከልቧ ኀዘን የተነሣ ምርር ብላ እያለቀሰች ወደ ጌታ ጸለየች።


ሳሙኤል እስኪ ነጋ ድረስ ተኛ፤ ከዚያም ተነሥቶ የጌታን ቤት በሮች ከፈተ፤ ራእዩንም ለዔሊ መንገር ፈራ፤


የእግዚአብሔር መብራትም ገና አልጠፋም ነበር፤ ሳሙኤል ደግሞ የጌታ ታቦት ባለበት፥ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ተኝቶ ነበር።


እዚያ እንደደረሰም፥ ዔሊ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ልቡ ስለ ተጨነቀ፥ በመንገድ ዳር ወንበሩ ላይ ተቀምጦ ይጠባበቅ ነበር። ሰውየውም ወደ ከተማው ገብቶ የሆነውን ሁሉ ባወራ ጊዜ፥ ከተማው ሁሉ በጩኸት ተናወጠ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች