ዕቃዬን አንድ በአንድ በርብረሃል፤ ታዲያ፣ የአንተ ሆኖ ያገኘኸው ዕቃ የትኛው ነው? ካለ፣ እስኪ በአንተም በእኔም ዘመዶች ፊት አቅርብና እነርሱ ያፋርዱን።
ኢያሱ 7:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከድንኳኑም አውጥተው፣ ኢያሱና እስራኤላውያን ሁሉ ወዳሉበት አምጥተው በእግዚአብሔር ፊት አኖሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከድንኳኑም ውስጥ ወስደው ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤል ልጆች ሁሉ አመጡት፤ በጌታም ፊት አኖሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱንም ከድንኳኑ በማውጣት፥ ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤላውያን አምጥተው በእግዚአብሔር ፊት አኖሩአቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከድንኳኑም ውስጥ አውጥተው ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ አመጡት፤ በእግዚአብሔርምፊት አኖሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከድንኳኑም ውስጥ ወስደው ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤል ልጆች ሁሉ አመጡት፥ በእግዚአብሔርም ፊት አኖሩት። |
ዕቃዬን አንድ በአንድ በርብረሃል፤ ታዲያ፣ የአንተ ሆኖ ያገኘኸው ዕቃ የትኛው ነው? ካለ፣ እስኪ በአንተም በእኔም ዘመዶች ፊት አቅርብና እነርሱ ያፋርዱን።
ኢያሱም ከመላው እስራኤል ጋራ ሆኖ፣ የዛራን ልጅ አካንን፣ ብሩን፣ ካባውን፣ የወርቁን ቡችላ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፣ የከብቱን መንጋ፣ አህዮቹንና በጎቹን እንዲሁም ድንኳኑንና የርሱ የሆነውን ሁሉ ወደ አኮር ሸለቆ አስወሰደ።