ሉቃስ 2:51 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ወደ ናዝሬት ሄደ፤ ይታዘዛቸውም ነበር፤ እናቱም ይህን ሁሉ ነገር በልብዋ ትይዘው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዐብሯቸው ወደ ናዝሬት ወረደ፤ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ሁሉ ነገር በልቧ ትጠብቀው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፤ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም እነዚህን ነገሮች ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም ጋር ሂዶ ወደ ናዝሬት ወረደ፤ ይታዘዝላቸውም ነበር፤ እናቱ ግን ይህን ሁሉ ነገር ትጠብቀው፥ በልብዋም ታኖረው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፥ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር። |
የሕልሙም ትርጒም እዚህ ላይ ይፈጸማል፤ እኔም ዳንኤል እጅግ ሐሳቡ አስፈራኝ፤ በመደንገጥም ፊቴ ገረጣ፤ ይሁን እንጂ ሁሉንም ነገር በልቤ ሰውሬ ያዝኩ።
ኢየሱስ ግን “የጽድቅን ሥራ ሁሉ በዚህ መንገድ መፈጸም ስለሚገባን፥ አሁንስ ተው፤ እንዲሁ ይሁን” ሲል መለሰለት። ዮሐንስም በነገሩ ተስማምቶ ኢየሱስን አጠመቀው።
ቀጥለውም “ለመሆኑ ይህ እንጨት ጠራቢው የማርያም ልጅ አይደለምን? የያዕቆብ፥ የዮሳ የይሁዳና የስምዖን ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ እዚህ ከእኛ ጋር አይደሉምን?” እያሉ በመናቅ ሳይቀበሉት ቀሩ።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ ‘አንተ ሐኪም፥ እስቲ ራስህን አድን፥’ የሚለውን ምሳሌ እንደምትጠቅሱብኝ እርግጠኛ ነኝ፤ እንዲሁም ‘በቅፍርናሆም አድርገሃል ሲሉ የሰማነውን ሁሉ፥ እዚህም በገዛ አገርህ አድርግ’ ትሉኛላችሁ።