Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 2:51 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

51 ከዚያም ዐብሯቸው ወደ ናዝሬት ወረደ፤ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ሁሉ ነገር በልቧ ትጠብቀው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

51 ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፤ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም እነዚህን ነገሮች ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

51 ከዚያም በኋላ ኢየሱስ ከእነርሱ ጋር ወደ ናዝሬት ሄደ፤ ይታዘዛቸውም ነበር፤ እናቱም ይህን ሁሉ ነገር በልብዋ ትይዘው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

51 ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ሂዶ ወደ ናዝ​ሬት ወረደ፤ ይታ​ዘ​ዝ​ላ​ቸ​ውም ነበር፤ እናቱ ግን ይህን ሁሉ ነገር ትጠ​ብ​ቀው፥ በል​ብ​ዋም ታኖ​ረው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

51 ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፥ ይታዘዝላቸውም ነበር። እናቱም ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 2:51
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወንድሞቹ ቀኑበት፤ አባቱ ግን ነገሩን በልቡ ያዘው።


አንተን እንዳልበድል፣ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።


“የነገሩ ፍጻሜ ይህ ነው፤ እኔም ዳንኤል በሐሳቤ እጅግ ተጨነቅሁ፤ መልኬም ተለዋወጠ፤ ይሁን እንጂ ነገሩን በልቤ ጠበቅሁት።”


ኢየሱስ ለሕዝቡ ሲናገር ሳለ፣ እናቱና ወንድሞቹ ሊያነጋግሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር።


ኢየሱስም፣ “ግድ የለም ፍቀድልኝ፤ ይህን በማድረግ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና” አለው፤ ዮሐንስም በነገሩ ተስማማ።


በዚህ ጊዜ ኢየሱስ የገሊላ ከተማ ከሆነችው ከናዝሬት መጥቶ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ።


ይህ ዐናጺው አይደለምን? የማርያም ልጅ፣ የያዕቆብ፣ የዮሴፍ፣ የይሁዳና የስምዖን ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ እዚሁ እኛው ዘንድ አይደሉምን?” ከዚህም የተነሣ ተሰናከሉበት።


እነርሱም፣ “የናዝሬቱ ኢየሱስ በዚህ እያለፈ ነው” ብለው ነገሩት።


ማርያም ግን ይህን ሁሉ ነገር በልቧ ይዛ ታሰላስል ነበር።


ዮሴፍና ማርያም በጌታ ሕግ የታዘዘውን ሁሉ ከፈጸሙ በኋላ፣ በገሊላ አውራጃ ወዳለችው ከተማቸው ወደ ናዝሬት ተመለሱ።


ከዚያም ወዳደገበት ከተማ ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ወደ ምኵራብ ገባ፤ ሊያነብብም ተነሥቶ ቆመ።


እርሱም፣ “ ‘ባለመድኀኒት ሆይ፤ ራስህን ፈውስ፤ በቅፍርናሆም ስታደርግ የሰማነውን ነገር እዚህ በራስህ ከተማ ደግሞ አድርግ’ የሚለውን ምሳሌ እንደምትጠቅሱብኝ ጥርጥር የለውም” አላቸው።


ለክርስቶስ ካላችሁ አክብሮታዊ ፍርሀት የተነሣ አንዳችሁ ለአንዳችሁ ተገዙ።


የተጠራችሁትም ለዚሁ ነው፤ ምክንያቱም ክርስቶስ ስለ እናንተ መከራን የተቀበለው የርሱን ፈለግ እንድትከተሉ ምሳሌን ሊተውላችሁ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች