መጽሐፈ ጥበብ 8:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የከበረ ደስታ ወዳጇ፥ የማያልቅ ሃብት የሥራዋ ፍሬ መሆኑን አወቅሁ፤ ተከታዮቼን በማስተማር ማስተዋልን፥ እርሷን በማነጋገር ዝናን ማትረፍ እንደሚቻል ተገነዘብሁ፤ እናም እርሷን ፈልጌ ለማግኘት ያልረገጥሁት መንገድ የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በፍቅሯም መልካም ደስታ አለ፤ በእጅዋ ሥራም የማያልቅ ብልጽግና አለ፤ በነገሯም ውስጥ የዕውቀት ትምህርት አለ፤ ከእርሷም ጋር አንድ በመሆን የሚያስመካ ነገር አለ፤ ለራሴም እወስዳት ዘንድ እየፈለግኋት ሀገሩን ዞርሁ። |