የሁሉም ጌታ ማንንም አይፈራምና፥ ታላቅነት እርሱን አያስደነግጠውም፤ ትንሹንና ትልቁን የፈጠረ፥ ለሁሉም የሚፈልገውን የሚሰጥ እርሱ ነውና።
እግዚአብሔር ፊት አይቶ አያዳላምና፤ የታላቁንም መከበር አያፍርምና፤ እንደዚሁም ታናሹንና ታላቁን ስለ ፈጠረ ለገዡና ለተገዡ ሁሉ ያስባል፤ ይወስንላቸዋልም።