ጻድቁ ግን በድፍረት ይቆማል፤ ጨቋኞቹን ግንባሩን ሳያጥፍ ይመለከታል፥ ስላሳለፈው መከራም አያስብም።
ያንጊዜ ጻድቁ፦ መከራ ባጸኑበትና ድካሙን በካዱ፥ ነገሩንም በናቁ ሰዎች ፊት በብዙ መገለጥ ይቆማል።