ቋሚውን ኃጢአተኛ፥ ፍጹምነትን ፈጥኖ ያገኘ ወጣት፥ ኃጢአተኛውን ሽማግሌ ይፈርድበታል።
ጻድቅ ሰው ከሞተ በኋላ በሕይወት ባሉ ክፉዎች ላይ ይፈርዳል። ጐልማሳ ሰውም ፈጥኖ በሚሞትበት ጊዜ የዐመፃ ሽምግልና ዕድሜአቸው በበዛ በክፉዎች ሰዎች ላይ ይፈርዳል።