የተመረጡት ሁሉ፥ ክብርና ምሕረት እንደሚጠብቃቸው፥ እርሱም ስለ እነርሱ እንደሚሟገት አልተከሠተለትም።
ልዩ የሆኑ ሰዎች ግን ይህን አይተው ልብ አላደረጉትም፤ የዚህንም ትርጓሜ በልባቸው አላሳደሩትም። የእግዚአብሔር ጸጋው ለጻድቃኑ ነውና የይቅርታው ጕብኝትም ለመረጣቸው ሰዎች ነውና።