በእርሱ የሚያምኑ እውነትን ያውቃሉ፤ ታማኞች የሆኑም፥ ክብርና ምሕረት የቅዱሳን ፈንታ ነውና፥ እርሱም ስለ እነርሱ ይቆማልና፥ በፍቅር ከእርሱ ጋር ጸንተው ይኖራሉ።
በእርሱ የሚያምኑ ሰዎች እውነትን ያውቃሉ፤ ጸጋና ምሕረት ለመረጣቸው ነውና፥ የተገለጠ ጕብኝቱም ለጻድቃኑ ነውና ምእመናን በእርሱ ፍቅር ጸንተው ይኖራሉ።