ጥበብ የሰው ልጅ ወዳጅ የሆነች መንፈስ ናት፤ ክፉ ተናጋሪን ግን ከስድቡ ነጻ አታደርገውም፤ እግዚአብሔር ለውስጣዊ ማንነቱ ምስክር ነውና፥ ልቡን በጥልቀት ይመለከታል፤ የአንደበቱንም ቃል ይሰማል።
ጥበብን የሚገልጽ መንፈስ ሰው ወዳጅ ነውና፥ በከንፈሩ የሚሳደበውንም አያነጻውም። እግዚአብሔር በኵላሊቶቹ ምስክር ነውና፥ ነዋሪ ጕበኛም ልቡናውን ይመረምረዋል፤ አንደበቱንም ይሰማዋል።