ወደ ሜዶን ደረሱ፥ ወደ አቅባጥናም ተቃረቡ።
መልአኩ አለው፥ “አንተ ወንድሜ! ዛሬ በራጉኤል ቤት እናድራለን፤ እርሱም ዘመድህ ነው፤ አንዲት ልጅም አለችው፤ ስሟም ሳራ ይባላል፤ ሚስት ትሆንህ ዘንድ እንዲሰጥህ ስለ እርስዋ እናገራለሁ፤ ለአንተ ውርሷ ይደርስሃልና።