ጦቢትም “እህቴ ሆይ እንዲህ ዓይነት ሐሳብ አታስቢ፥ በደኅና ሄዶ በደኅና ይመለሳል፥ አንቺም በደኅና መመለሱን በዓይንሽ ታያለሽ፥ እንዲህ ዓይነት ሐሳብ አታስቢ፥ ስለ እነርሱም አትጨነቂ፤
ቸር መልአክ በፊቱ ይሄዳልና፥ ጎዳናውንም ያቃናለታልና፥ በደኅናም ይመለሳልና።”