ፍየልዋ ወደ ቤቴ በመጣች ጊዜ መጮህ ጀመረች፤ እኔም ሚስቴን ጠራሁና “ይህች ፍየል ከየት መጣች? ምናልባት በስርቆት መጥታ ይሆናል፥ ወደ ባለቤቶችዋ መልሰሽ ውሰጃት፤ በስርቆት የመጣ ነገር መብላት አንችልምና” አልኳት።
ወደ እኔም በመጣች ጊዜ ትጮህ ጀመር፤ እኔም እንዲህ አልኋት፥ “ይቺ ጠቦት ከወዴት ናት? የሰረቅሻት ከሆነችም ወደ ጌቶችዋ መልሻት። የተሰረቀ መብላት አግባብ አይደለምና።”