ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 2:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 እርሷም “ከደሞዜ በተጨማሪ የተሰጠችኝ ሥጦታ ናት” አለችኝ። እኔ ግን አላመንኳትም፥ ለባለቤቶችዋ እንድትመልስ ነገርኳት፥ በእስዋም በጣም አፈርሁ፤ እርሷም “አንተ ያደረግሃቸው ምጽዋቶች የት አሉ? መልካም ሥራዎችህስ ሁሉ የት አሉ? እነዚህን በጎ ተግባራት በመፈጸምህ ያገኘኸው ምን እንደሆነ ሁሉም ሰው ያውቃል።” ስትል መለሰች። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 እርሷም አለችኝ፥ “በደመወዜ ላይ ሰጡኝ፤” እኔ ግን አላመንኋትም፤ ለባለቤቶቹም መልሺ ብዬ ከእርሷ ጋር ተከራከርሁ፤ እርሷም መልሳ፥ “ጸሎትህና ምጽዋትህ ወዴት ነው? እነሆ በላይህ ያለው ሁሉ ታወቀ” አለችኝ። ምዕራፉን ተመልከት |