የዓይኑን ብርሃን ሲያጣ ዕድሜው ስልሳ ሁለት ዓመት ነበር። ከተፈወሰ በኋላ በምቾት፥ ምጽዋት በመስጠት፥ ያለማቋረጥ እግዚአብሔርን በማመስገንና ትልቅነቱንም በማክበር ኖረ።
ዐይኑም በጠፋ ጊዜ አምሳ ስምንት ዓመት ሆኖት ነበር። ከስምንት ዓመት በኋላም አየ፤ ምጽዋትም መጸወተ፤ ጌታ እግዚአብሔርን መፍራትንም ጨመረ፤ በእርሱም አመነ።