የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መጽ​ሐፈ ጦቢት 10:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አሁን በቅርቡ ይመጣል።” እርሷ ግን “ተወኝ፥ እኔን ማታለል ይቅርብህ፥ ሞቷል” በማለት መሰለችለት። ዓይኗን እንጂ ማንንም ስለማታምን ልጇ የሄደበትን መንገድ ለመመልከት በየቀኑ ፈጥና ትወጣ ነበር። ፀሃይ ስትጠልቅ ወደ ቤትዋ ትመለስ ነበር፤ ሌሊቱን ሙሉ እያዘነችና እያለቀሰች ታድር ነበር፥ እንቅፍል አይወስዳትም ነበር። ራጉኤል ለልጁ ሲል ምሎ የወሰናቸው ዐሥራ አራት የሰርግ ቀኖች እንዳልፉ፥ ጦብያ ወደ እርሱ ሄደና እንዲህ አለው “እንድሄድ ፍቀድልኝ አባትና እናቴ ከእንግዲህ ወዲህ አናየውም ብለው ተስፋ ቆርጠው ይሆናል፤ ስለዚህ እባክህ አባቴ እንድሄድ ፍቀድልኝ፥ ወደ አባቴ ቤት ልመለስ፥ በምን ሁኔታ ላይ እንደተውኩት አስቀድሜ ነግሬሃለሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሷም አለ​ችው፥ “አን​ተም ዝም በል፤ አታ​ታ​ለኝ፤ ልጄስ ሞት​ዋል።” ታለ​ቅ​ስ​ለ​ትም ዘንድ በሄ​ደ​በት ጎዳና ሁል​ጊዜ ትሄድ ነበር። የሰ​ርጉ በዓል ሳያ​ልቅ እን​ዳ​ይ​ሄድ ራጉ​ኤል ያማ​ለው ዐሥራ አራቱ የበ​ዐ​ዓል ቀን እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ ለል​ጅዋ ለጦ​ብያ እያ​ለ​ቀ​ሰ​ች​ለት በቀን እህል አት​በ​ላም ነበር፤ በሌ​ሊ​ትም ዝም አት​ልም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት



መጽ​ሐፈ ጦቢት 10:7
0 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች