ከዚህ በኋላ አሂካር አማለደኝና ወደ ነነዌ እንድመለስ ተፈቀደልኝ። በአሦር ንጉሥ በሰናክሬም ጊዜ አሂካር የወይን ጠጅ ቀጂዎች አለቃ፥ የመንግሥት ማኀተም ጠባቂ፥ የገንዘብ ቤቱ አስተዳዳሪና ነበር። ንጉሡ ኤሳራዶንም በዚህ በሥራው ላይ በድጋሚ ሾመው። እርሱም ዘመዴ የወንድሜ ልጅ ነበር።
አኪአኪሮስም ማለደልኝ፤ ወደ ነነዌም መለሰኝ። አኪአኪሮስም የማኅተምና የቤቱ ንብረት ጠባቂ ነበር። አስራዶንም ዳግመኛ ሾመው።