ከነነዌ ሰዎች አንዱ ወደ ንጉሡ ሄዶ የሰዎቹን ሬሳ በምሥጢር የቀበርሁ እኔ መሆኔን ተናገረ፤ ንጉሡ ስለ እኔ ማወቁንና እኔም ለመገደል እየተፈለግሁ መሆኑን ስገነዘብ ፈራሁና ሸሸሁ።
ከነነዌ ሰዎችም አንዱ ሰው ሄዶ እንደ ቀበርኋቸው ነገር ሠርቶ ከንጉሡ ጋር አጣላኝ፤ እኔም ተሰወርሁ፤ ሊገድሉኝ እንደሚፈልጉኝም ባወቅሁ ጊዜ ፈርቼ ገለል አልሁ።