በየትኛውም ቦታ፥ የታላላቅ ሥራዎችን ፈጣሪ፥ ከእናታችን ማሕፀን ጀምሮ ሕይወታችንን የታደገውን፥ በምሕረቱም የሚጠብቀንን፥ የሁሉንም አምላክ አመስግኑ።
አሁንም በሁሉም ቦታ ብዙ ተአምራት የሚያደርገውን፥ ከእናታችን ማኅፀን ጀምሮ ዘመናችንንም የሚያረዝመውን፥ እንደ ቸርነቱም ይቅርታውን የሚያደርግልንን፥ የሁሉን ፈጣሪ አመስግኑት።