እርሱም ወደ ታች ወርዶ፥ በመላው እሥራኤል ጉባኤ ላይ እጆቹን ያነሣል፥ ስሙን ለመጥራት ታድሏልና የጌታ ቡራኬም በአንደበቱ ይናገራል።
ከዚህም በኋላ እርሱ ወርዶ የእግዚአብሔርን በረከት በአንደበቱ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በስሙም ይመኩ ዘንድ በእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ ላይ እጁን አነሣ።