ጌታ ግን መሐሪ ነው፥ ቃሉን አያጥፍም፥ ለመረጠው ዘር አይነሣም፥ የወደደውንም ሰው ዘር አያጠፋም። እነሆ ለያዕቆብ ምትክ ተወለት፥ ለዳዊትም ከእርሱ የሚወጣ ሥር ሰጠው።
እግዚአብሔር ግን ቸርነቱን አልተወም፤ ሥራውንም አላጠፋም፤ የጻድቃኑንም ልጆች አልደመሰሰም፤ የሚወዱትንም ሰዎች ዘር አላጠፋም፤ ለያዕቆብም ቅሬትን ሰጠው፥ ከእርሱም ለዳዊት ሥርን ሰጠው።