የነነዌ ልጅ ኢያሱ፥ ጦረኛ፥ በትንቢትም ሥራ ሙሴን የተካ ነበር፥ እንደ ስሙ ሁሉ የሕዝብ አዳኝ በጠላቶቹ ላይ የበቀል ቅጣትን ያወረደ፥ እሥራኤልንም ለርስቱ ያበቃ ነው።
የነዌ ልጅ ኢያሱም በሰልፍ ውስጥ ጽኑዕ ነው። ከሙሴም ቀጥሎ ትንቢት ተናገረ፤ እንደ ስሙም ታላቅ ሆነ፤ እግዚአብሔር የመረጣቸውንም ከመከራ አዳናቸው፤ ለእስራኤል ምድራቸውን ያወርሳቸው ዘንድ ጠላቶቻቸውን ተበቅሎ አጠፋ።